የአንዳንድ የትራንስፖርት መጫኛ እና ማውረጃ ቦታዎች መቀየሩን፤ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ተናግሯል፡፡
ቢሮው የመጫኛ እና የማውረጃ ቦታዎችን ቀይሬአለው ያለው በመገናኛ አገልግሎት ሲሰጥባቸው የነበሩት ላይ ሲሆን በዚህም:-
በቦሌ ክፍለ ከተማ ፊት ለፊት ሲሰጥ የነበረው፤ ከመገናኛ - ቱሉ ዲምቱ እና ኮዬ ፈቼ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው መስመሮች አምቼ አጠገብ (ቀደም ሲል ከነበረበት ቦታ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ዝቅ ብሎ) ተቀይሯል፡፡
መገናኛ ውስጥ ተርሚናል ሲሰጡ የነበሩ፤ ከመገናኛ - ቃሊቲ፣ ከመገናኛ - ሳሪስ፣ ከመገናኛ - ጋርመንት መስመሮች በጊዜያዊነት መገናኛ ሙሉጌታ ህንጻ ዝቅ ብሎ አምቼ ፊት ለፊት መንገድ ተዛውሯል፡፡
ከዚህ በፊት ሙሉጌታ ህንፃ አካባቢ ይሰጡ የነበሩ መስመሮች (ከመገናኛ - ገርጂ፣ ከመገናኛ - ጎሮ፣ ከመገናኛ - አያት እና ከመገናኛ - ሰሚት የመጫኛና መውረጃ መስመሮች ወደ ዘርፈሽዋል አካባቢ በተዘጋጀው ጊዜያዊ ተርሚናል ውስጥ በመዛወር በሁሉም ሞዳሊቲ አገልግሎት መስጠት ጀምሬአለሁ ብሏል የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ።
留言