ጥቅምት 23፣2017 - በአንድ ክልል ብቻ ከ600,000 በላይ ሰዎች በወባ በሽታ ተይዘዋል
- sheger1021fm
- Nov 2, 2024
- 1 min read
ከዓመታት በፊት የመጥፋት ደረጃ ላይ ተቃርቦ እንደነበር የሚነገርለት #የወባ_በሽታ ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ ወረርሽኝ ደረጃ ላይ መድረሱን የዘርፉ ባለሞያዎች እየተናገሩ ነው፡፡
በአማራ ክልል በአንድ ሳምንት ብቻ ከ64,000 በላይ ሰዎች በወባ ወረርሽኝ እንደተያዙ ተነግሯል፡፡
በኦሮሚያ፣ በደቡብና በሌሎች አካባቢዎች ያለውም የበሽታው ስርጭት በተመሳሳይ ከፍተኛ ቁጥር በመያዝ ወረርሽኝ መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡
ይህ እንዴትና ለምን ሆነ? ስንል የተለያዩ ክልሎች የጤና ቢሮዎችን አነጋግረናል፡፡
ፋሲካ ሙሉወርቅ
Comments