top of page

ጥቅምት 23፣2016 -ዶክተር ለገሰ ቱሉ ረሃብ እነደተከሰተ የሚነገረው ወሬ ሀሰት ነው ቢሉም የተለያዩ ሹሞች ሰዎች በረሃብ እየሞቱ መሆኑን እየተናገሩ ነው

የመንግስት የኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሚንስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ በኢትዮጵያ ረሃብ የተከሰተባቸው ቦታዎች እንዳሉ ተደርጎ የሚነገረው ወሬ ሀሰት ነው ሲሉ አስተባብለዋል፡፡


ድርቅ እንጂ ረሃብ የለምም ይላሉ፡፡


ይሁንና ሸገር ያነጋገራቸው የተለያዩ አካባቢዎች የመንግስት ሹሞች በረሃብ ምክንያት የሰዎች እና የእንሰሳት ህይወት እያለፈ መሆኑን እየተናገሩ ነው፡፡


ረሃብ ላይ ነን የሚሉ ተፈናቃዮችም በርካታ ናቸው፡፡


ያሬድ እንዳሻው

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

Comments


bottom of page