ጥቅምት 22፣2017 - ‘’2016/17 የመኽር እርሻ ወቅት 20.4 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በዘር ተሸፍኗል’’ ግብርና ሚኒስቴር
- sheger1021fm
- Nov 1, 2024
- 1 min read
‘’2016/17 የመኽር እርሻ ወቅት 20.4 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ታርሶ በዘር ተሸፍኗል’’ ሲል ግብርና ሚኒስቴር ተናገረ።
በዘር የተሸፈነው 20 ሚሊዮን 235,000 ሄክታር መሬት ነው።
ከዚህ ውስጥ በቆላማው የሀገሪቱ አካባቢ እስካሁን 1.7 ሚሊየን ሄክታር ላይ የተዘራ ሰብል ተስብስቦ 5.33 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ተሰብስቧል።
በመኽር እርሻ 608 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ይገኛል ተብሎም ይጠበቃል።
በመኽር ወቅት በጥጥ፣ ሆልቲ ከልቸር እና ሰፋፊ እርሻ ሲደመር በመኽር ወቅት የታረሰው መሬት 22 ሚሊየን ሄክታር ይደርሳል ተብሏል።
በመኽር ከታረሰው ውስጥ 11.8 ሚሊየን ሄክታር መሬት በዘር የተሸፈነው በክላስተር ሲሆን ከታረሰው መሬት ውስጥ 25 ከመቶ ወይም 5 ሚሊየን 49,000 ሄክታር የሚሆነው መሬት የታረሰው በትራክተር ነው ሲሉ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) ተናግረዋል።
በ2017/18 የምርት ዘመን 2 ሚሊየን ኩንታል ምርጥ ዘር ለማቅረብ ታቅዷል ተብሏል።

በ2017/18 የግብርና ስራ የግብርና ሚኒስቴር 24 ሚልየን ኩንታል ማዳበርያ ለመግዛት እንቅስቃሴ ጀምሯል ያሉት ዶክተር ግርማ አመንቴ የመጀመርያው መርከብ ጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ ጅቡቲ ይደርሳል ሲሉ አስረድተዋል።
መንግስት ለድጎማ የሚሆን 53 ቢሊየን ብር መያዙንም ሰምተናል።
ለማዳበርያ ግዢው 1.3 ቢሊየን ዶላር መንግስት ፈቅዷል።
በ2016/17 የግብርና ስራ 8.2 ሚሊየን ሄክታር መሬት በስንዴ ይሸፈናል ተብሏል፡፡
4 ሚሊየን ሄክታር የሚሆነው በመኽር፣ 4.2 የሚሆነው ደግሞ በበጋ መስኖ ልማት እንደሚመረት ተነግሯል፡፡
ከዚህም 300 ሚሊየን ኩንታል ምርት ይሰበሰባል ተብሎ መታቀዱን የግብርና ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
እስካሁን ድረስ 850,000 ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ ለመሸፈን የታረሰ ሲሆን 500,000 የሚሆነው በዘር ተሸፍኗል።
በ2017 በጀት ዓመት የግብርና ሚኒስቴር 1.4 ቢሊየን ኩንታል ምርት እሰበስባለሁ ብሎ ማቀዱን ሚንስትሩ ግርማ አመንቴ ሲናገሩ አድምጠናል።
በረከት አካሉ
Comments