top of page

ጥቅምት 22፣2017 - ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ተፈጥሮአዊ አደጋዎች ሲደጋገሙ እየታየ ነው

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ተፈጥሮአዊ አደጋዎች ሲደጋገሙ እየታየ ነው፡፡


የመሬት መንቀጥቀጥ፣ የመሬት መንሸራተት እና ጎርፍ እየተስተዋሉ ነው፡፡


ባለፈው ክረምት በጎፋ ዞን የደረሰው የመሬት መንሸራተት ያስከተለው ጉዳት እና የሞተው ሰው ከከዚህ ቀደሙ ተመሳሳይ አደጋዎች ሁሉ ከፍተኛው ነው ተብሎለታል፡፡


እንዲህ ያሉ ተፈጥሮአዊ አደጋዎችን ቀድሞ ለመከላከል የሚያስችል የቴክኖሎጂ አቅም አለመኖሩ ደግሞ ችግሩን የከፋ እንዳደረገው ሲነገር ቆይቷል፡፡


አሁን ሳይንስ ረቮሉሽን ኧርዝ (Scientific Revolution Earth) የተሰኘ ተቋም ይዞት የመጣው ቴክኖሎጂ ለዚህ ችግር መላ የሚሆን ይመስላል፡፡

ተቋሙ የመሬት መንቀጥቀጥ እና ጎርፍ የመሳሰሉ አደጋዎች ከመከሰታቸው በፊት ቀድሞ ማስጠንቀቂያ የሚሰጥ ቴክኖሎጂ አምጥቻለሁ ብሏል፡፡


በኢትዮጵያ በቅርቡ ስራ ላይ ይውላል ተብሎ የሚጠበቀው ይሄው ቴክኖሎጂ የወንዝ ተፋሰስ ባለባቸው እና የመሬት መንቀጥቀጥ በሚከሰትባቸው ቦታዎች በመትከል፤ በአደጋ ጊዜ ቅድመ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጥ የሚያደርግ ነው ተብሎለታል፡፡


በተጨማሪም ለአደጋ ስጋት ተከላካዩች ጭምር የማስጠንቀቂያ ደውል የሚሰጥ መሆኑን ለሸገር ራዲዮ የተናገሩት የድርጅቱ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሳሙኤል ከፈለኝ ከተለያዩ ተቋማት ጋር ለመስራት ዝግጅታችንን አጠናቀናል ብለዋል፡፡


በዚህም መሰረት ቴክኖሎጂው ወደ ተግባር እንዲገባ እና እንድንገለገልበት ተቋማት ወደ እኛ መጥተው አብረውን ለመስራት ፍቃደኛ መሆን አለባቸው ብለዋል፡፡

Comments


bottom of page