ጥቅምት 22፣2017 - ትምህርት ቤቶች ከ1ኛ ደረጃ ትምህርት ጀምሮ፤ የግብረገብ ትምህርት ማስተማር እንደሚኖርባቸው የሚደነግግ ህግ ተረቀቀ
- sheger1021fm
- Nov 1, 2024
- 1 min read
ትምህርት ቤቶች ከ1ኛ ደረጃ ትምህርት ጀምሮ፤ የግብረገብ ትምህርት ማስተማር እንደሚኖርባቸው የሚደነግግ ህግ ተረቀቀ፡፡
እንደ አንድ መሰረታዊ የትምህርት አይነት ከ1ኛ ክፍል ጀምሮ እስከ 6ኛ ክፍል ሁሉም ትምህርት ቤቶች የግብረገብ ትምህርትን እንዲያስተምሩ የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡
በተጨማሪወም ረቂቅ አዋጁ ተማሪዎች ቢያንስ 3 ቋንቋን እንዲማሩ ይደነግጋል፡፡
የአፍ መፍቻ ቋንቋን ከቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ጀምሮ እንደሚሰጥ ረቂቁ ያስረዳል፡፡
የአፍ መፍቻ ቋንቋ ከ1ኛ ክፍል ጀምሮ ደግሞ እንደ አንድ የትምህርት አይነት እንዲሁም እንደ ማስተማሪያ ቋንቋ ሊያገለግል እንደሚችል ተጠቅሷል፡፡
ትዕግስት ዘሪሁን
Comments