top of page

ጥቅምት 22፣2017 - ባንኮች እርስ በርእሳቸው የሚበዳደሩበት የገንዘብ ገበያ ይፋ ማድረጉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተናገረ

በባንኮች እርስ በርእሳቸው የሚበዳደሩበት የገንዘብ ገበያ ይፋ ማድረጉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተናገረ።


ማዕከላዊ ባንኩ ባወጣው መግለጫ ነው ባንኮች እርስ በርሳቸው የሚበዳደሩበት የገንዘብ ገበያ ይፋ ማድረጉን የተናገረው።


በባንኮች መካከል የሚደረግ #የገንዘብ_ገበያ መጀመር፤ ንግድ ባንኮች የዕለት ተዕለት የገንዘብ ፍሰታቸውን በአግባቡ እንዲያስተዳድሩ ይረዳቸዋል ተብሏል።


በተጨማሪም የገንዘብ እጥረት ስጋት እንደሚቀንስ እና የተረጋጋ #የወለድ_ተመን እንዲኖር ያስችላል ሲል ብሔራዊ ባንኩ ተናግሯል።


ባንኩ ይፋ ያደረገው አሰራር የሚከተሉት ነጥቦች የሚያካትት መሆኑንም ጠቁሟል።


በዚህ የግብይት መድረክ፤ ንግድ ባንኮች የአጭር ጊዜ (ለአንድ ቀን ወይም ለሰባት ቀናት) መቆየት የሚችል ገንዘብ መበደርና ማበደር ይችላሉ ተብሏል።


በባንኮች መካከል የሚደረግ የወለድ ተመንም፤ ብሔራዊ ባንክ ባስቀመጠው የፖሊሲ የወለድ ተመን  ክልል ውስጥ መሆን እንዳለበት ተጠቅሷል።


በባንኮች መካከል የሚደረግ የገንዘብ ግብይት በኢትዮጵያ #ሰነደ_ሙዓለ_ንዋይ ገበያ የግብይት መድረክ ላይ ብቻ እንደሚሆንም ባንኩ አስረድቷል።


በባንኮች መካከል የሚደረግ የገንዘብ ግብይት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው የገንዘብ መመሪያ እና የስነ ምግባር ደንብ መሰረት መከናወን እንዳለበትም ተነግሯል።


በእርስ በእርስ የገንዘብ ግብይቱ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉም ባንኮች የሚጠበቅባቸውን መስፈርቶች በማሟላት ከብሔራዊ ባንክ #ፈቃድ ማግኘት ይኖርባቸዋልም ተብሏል።


በተጨማሪም ሁሉም ንግድ ባንከች አዲሱን የገንዘብ ግብይት ላይ በንቃት እንዲሳተፉ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መክሯል።


ማንያዘዋል ጌታሁን

Comments


bottom of page