ጥበቃ የሚሹትና የቤተሰብ ክትትል የሚያስፈልጋቸው ህፃናት በቀላሉ ለጥቃት ተጋላጭ ይሆናሉ፡፡
ለህጻናት ተስማሚ የፍትህ ሥርዓት እንዲኖር ችሎቶች ማደራጀት ላይ የተከወኑ ስራዎች ቢኖሩም ምን ያህሉ ጉዳትና ጥቃት የደረሰባቸው #ህፃናት ወደ ፍትህ ሥርዓቱ ይመጣሉ?
የሚሰጡት ውሳኔዎችስ ምን ያህል በቂ ናቸው የሚለው ጥያቄ ያስነሳል፡፡
ለጥቃት ተጋላጭ የሆኑ ህፃናት ወደ #ፍትህ ተቋማት ሲቀርቡ ደህንነታቸውን ከመጠበቅ አኳያ ምን ያህል መሻሻሎች አሉ ስንል ጠይቀናል፡፡
እርጎዬ ካሣ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የካ ምድብ በሴቶች እና ህጻናት ላይ የሚያገለግሉ ዳኛ ናቸው፡፡
ወደ ችሎት ከሚመጡ ጉዳዮች ውስጥ በህፃናት ላይ የሚፈጸም ወሲባዊ እና አካላዊ ጥቃት እንዲሁም አሁን ላይ በርከት እያሉ የመጡት የህጻናት ጉልበት ብዝበዛ ወንጀሎችን በመጥቀስ ወደ ህግ የመጡት ቅጣት እንዲያገኙ ተደርጓል ይላሉ፡፡
ወደ ህግ የሚመጡትን ያህል ብዙ በህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ደግሞ ተድበስብሰው የሚቀሩ በመሆኑ ውሳኔዎቹ አስተማሪ እንዲሆኑ ማድረግ ያስፈልጋል ተብሏል፡፡
በኢትዮጵያ ካሉ ህጻናት ግማሽ ያህሉ እድሜያቸውን የማይመጥን የጉልበት ስራ እንዲሰሩ የሚገደዱ ሲሆን በሀገሪቱ የተከሰቱ ግጭቶች መበርከት ደግሞ ቀድሞውንም የነበረውን በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደርሱ #ጥቃቶች እንዲባባሱ ማድረጋቸው ተነግሯል፡፡
ለዚህም በፍትህ ሥርዓቱ ወንጀለኞችን ለመቅጣት የሚሰጡ ውሳኔዎች ክፍተት ያለባቸው መሆኑ ለወንጀሎቹ መባባስ ምክንያት ነው ተብሏል፡፡
ምህረት ስዩም
댓글