top of page

ጥቅምት 22፣2016 - የቱሪዝም ዘርፉን ለማዘመን መንግስት አጥብቄ እየሰራሁ ነው አለ

የቱሪዝም ሚኒስቴር ለተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች ሀገሪቱ ያላትን የቱሪዝም ሀብት ባስተዋወቀበት ፕሮግራም ተገኝተን ነው ይህንን የሰማነው።


የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ አቶ ስለሺ ግርማ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራባቸው ካሉ ዘርፎች የቱሪዝም ዘርፉ አንዱ ነው ብለዋል።


የቱሪዝም ሚኒስቴር ለሚቀጥሉት አስርት ዓመታት ለመስራት የሚያልመው ስራ ከወዲሁ አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ነው ተብሏል።


ሀገሩቱ እንደአለም አቀፍ በርካታ ቅርሶችን በዩኔስኮ አስመዝግባለች ያሉት ሚኒስትር ድኤታው አሁን በአለም ምርጡ መዳረሻ መሆን እንፈልጋለን ብለዋል።


ይህንን ለማሳካት ለኢንቨስተሮች በራችን ክፍት ነው ብለዋል።

በቱሪዝሙ ዘርፍ ለሚሰማሩ ኢንቨስተሮች መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀቱን አቶ ስለሺ ተናግረዋል።


መንግስት ከተለያዩ ሀገራት ኢምባሲዎች ጋር የቱሪዝሙን ዘርፍ ለማስተዋወቅ እየሰራ ነው ቢባልም ከነማን ጋር እየተሰራ እንደሆነ ግን አልተጠቀሰም።


ኢንቨስተሮች በየለያዩ የቱሪዝም አገልግሎት መስጫ ስራዎች ላይ በመሰማራት ኢንቨስት እንዲያደርጉ ተጠይቋል።


ሀገሪቱ የተላያዩ የቱሪዝም መደረሻዎች እና ታሪካዊ ስፍራዎችና ውብ የሆነ ባህል አሏት ያሉት ተሳታፊ ዲፕሎማቶች አብረው ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው በውይይቱ ተናግረዋል።


የቱሪዝም ሚኒስቴር ከሁሉም ኢምባሲዎች ጋር ለመስራት እና በቱሪዝም ሴክተሩ ለሚሰማሩ ኢንቨስተሮች ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀቱን በመድረኩ ሲነገር ሰምተናል።



በረከት አካሉ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page