ከኢንዱስትሪ መስክ በዚህ ዓመት 12.8 በመቶ እድገት ይጠበቃል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ፡፡
‘’አሁን ላይ የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም 67 በመቶ ማድረስ ተችሏል’’ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‘’የኢንዱስትሪ ዘርፉም በተያዘው በጀት ዓመት 12.8 በመቶ እንደሚያድግ ይጠበቃል’’ ብለዋል፡፡
በዚህም ከአምራች ዘርፍ 12 በመቶ እድገት፣ እንዲሁም ከኮንስትራክሽን መስክም 12.3 በመቶ እድገት ይጠበቃል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡
‘’ኢንዱስትሪ በዚህ ዓመት ይህን ያህል እድገት የሚመጣው የተጀመረው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ውጤት እያመጣ ስለሆነ ነው’’ ተብሏል፡፡
ከፋበሪካዎች ጋር የሚያያዝ መብራት፣ ቴሌኮም፣ የመሬት አቅርቦት እና ከባንክ ጋር የሚያያዙ ችግሮች ከሞላ ጎደል ተቀርፈዋል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፡፡
አሁን ኢንዱስትሪዎች የሚፈልጉት ከጉሙሩክ ጋር የሚያያዝ ስራ እንደሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመው ለዚህም ስራ ተጀምሯል ብለዋል፡፡
በዚህም ዓመት ከፋብሪካ በላይ የሆኑ 72 ፕሮጀክቶች ወደ ገበያ እንደሚገቡም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
Comments