ኩባንያዎቹ ለዚሁ ስራ አንዲሆን በአዲስ አበባ ጌቱ ኮሜርሻል ህንጻ ላይ ምርት ማሳያ ቦታ ከፍተዋል፡፡
ኢሼሎን ግሩፕ የኢትጵያዊያን እና ካናዳዊያን ድርጅት ሲሆን በኢኮሜርስ፣ መጋዘን፣ ሎጅስቲክስ፣ ግብርና እና ማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች ላይ የሚሰራ ኩባንያ ነው፡፡
ኢሼሎን ግሩፕ ከአሊ ኤክስፕረስ በፈጠሩት ጥምረት በኢትዮጵያ የኦንላይን ግብይት የበለጠ ተደራሽ፣ አስተማማኝ እና ቀልጣፋ ማድረግ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡
በዚህ አጋርነት፣ ኢሼሎን ግሩፕ በኢትዮጵያ ያለውን ልምድና ስም በመጠቀም የሀገሪቱን የኢ-ኮሜርስ እድገትን ለማፋጠን ይሰራል ተብሏል፡፡
የሁለቱ ኩባንያዎች ትብብር አዲስ አበባ ውስጥ የኤሌክትሮኒክስ ግብይትን ተግባራዊ ማድረግ የሚቻልበትና ድንበኞችም በአካል ሄደው የሚያዩት የምርት ማሳያ ክፍል ማቋቋምን ያካትታል ተብሏል።
ይህም ደንበኞችን፤ ምርቶችን መፈተሽ እና በቦታው ላይ ድጋፍ የሚያገኙበት አዲስ ሁኔታን ስለሚፈጥር በባህላዊ እና የዲጂታል ንግድ መካከል ያለውን ልዩነት ያጠባል ተብሎ ተነግሮለታል።
ኢሼሎን ግሩፕ ከአሊ ኤክስፕረስ ጋር በመተባበር በኢትዮጵያን ገበያ ስራ መጀመራቸው
ከውጪ ሀገር እቃ የሚያስመጡ ነጋዴዎች ውጪ ሀገር መጓዝ ሳይጠበቅባቸው በኦልላይን የሚያዙትን እቃ አዲስ አበባ በተከፈተው ማሳያ ቦታ አይተው ትዕዛዝ መስጠት ያስችላቸዋልም ተብሏል፡፡
"የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እድገት ሞያውን በጠበቀ፣ በታማኝነት እና በብቃት ለማበርታት ቁርጠኛ ነን። ከከአሊ ኤክስፕረስ ጋር ያለን አጋርነት ከዚህ ራዕይ ጋር የተጣጣመ ነው፣ ለኢትዮጵያዊያን ስራ ፈጣሪዎች ብዙ እድሎችን እና ለተጠቃሚዎች የበለጠ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል”ሲሉ የኢሼሎን ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሚካኤል ማሞ ተናግረዋል።
ከኢሼሎን ግሩፕ ጋር በመሆን በኢትዮጵያ የኢኮሜርስ ገበያ ውስጥ የገባው አሊ ኤክስፕረስ በኢባባ ግሩፕ ስር ያለ ድርጅት ሲሆን ዋነኛ ስራውም የኦንላይን ግብይት ነው፡፡
Comments