top of page

ጥቅምት 21፣2017 - ''አንዳንዶቹ ኤምባሲዎች ጥቁር ገበያ ማሯሯጥ ውስጥ የሚሳተፉ አሉ’’ ጠ/ር ዐቢይ አህመድ

‘’መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ ኤምባሲዎች መካከል አንዳንዶቹ የጥቁር ገበያ ማሯሯጥ ውስጥ የሚሳተፉ አሉ’’ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ


“አንዳንድ ኤምባሲዎች የኢትዮጵያ ሀብት የመዝረፍ እና #የውጪ_ምንዛሪ_ቢዝነስ የሚሰሩ ኤምባሲዎች አሉ” አሉ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡


‘’እነዚህ ኤምባሲዎች ላይ ጥብቅ ክትትል ይደረጋል፤ የማይታረሙ ከሆነ ግን #ጥብቅ እርምጃ ይወዳል’’ ሲሉም አስጠንቅቀዋል፡፡


“ጤናማ ዝምድና የማያደርግ ማንንም ኤምባሲ እኛ አንፈልግም፣ እኛ የምንፈልገው ጤናማ፣ ህጋዊ ሥርዓት ያለው መንገድ የሚከተል ብቻ ነው” ብለዋል፡፡


“ያን ስራ የሚሰሩ፣ ነገር እንዳይበላሽ የታገስናቸው፣ ስራቸው ግን የብላክ ማርኬት ማሯሯጥ የሆኑ ኤምባሲዎች አሉ ሲሉ” አስረድተዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፡፡

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page