top of page

ጥቅምት 21፣2017 - በ2017 ዓመት 8.4 በመቶ እድገት ይመዘገባል ተብሎ አንደሚጠበቅ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ተናገሩ

በ2017 በጀት ዓመት 8.4 በመቶ እድገት ይመዘገባል ተብሎ አንደሚጠበቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ፡፡


ባሳለፈነው 2016 በጀት ዓመትም በኢትዮጵያ 8.1 በመቶ እድገት ተመዝግቧል ብለዋል፡፡


‘’ይህ በዓለም አቀፍ ደረጃም ትልቅ ስኬት ነው’’ ሲሉም ተደምጠዋል፡፡


‘’በዘንድሮው በጀት ዓመት ደግሞ 8.4 በመቶ እድገት ይመዘገባል’’ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህም ውስጥ ግብርና 6.1 በመቶ እንደሚያድግ ተናግረዋል፡፡


በበጀት ዓመቱ 30 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በማረስ 1.4 ቢሊዮን ኩንታል ምርት ይጠበቃል ሲሉ አስረድተዋል፡፡


በዚህ ዓመት ክረምት እና በጋ 8.2 ሚሊየን ሄክታር መሬት በስንዴ ምርት ይሸፈናል፤ ከዚህም 300 ሚሊየን ኩንታል ምርት እንጠብቃለን ብለዋል፡፡


ሰሊጥ፣ ለውዝ፣ አኩሪ አተር እና ሌሎችም ቀድሞ ከነበራቸው የምርት ሁኔታ ጨምሯል ሲሉ አስረድተዋል፡፡


ንጋቱ ሙሉ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page