ጥቅምት 21፣2017 - ‘’መንግስት እስካሁን የሰላም እና የጸጥታን ችግርን ለመፍታ እየሄደ ያለው በወታደራዊ መንገድ ነው፤ ለምን ፖለቲካዊ መንገድን አልደፈረም’’ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባል
- sheger1021fm
- Oct 31, 2024
- 1 min read
‘’መንግስት እስካሁን የሰላም እና የጸጥታን ችግርን ለመፍታ እየሄደ ያለው በወታደራዊ መንገድ ነው፤ ለምን ፖለቲካዊ መንገድን አለደፈረም’’ ሲሉ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባል ጠየቁ፡፡
‘’በመላው ሀገሪቱ ያለው ጅምላ፣ የንጹሃን ግድያ፣ ህግወጥ እስራት፣ ጾታዊ ጥቃት፣ ህገ ወጥ ቤት ፈረሳ አሁንም እንደ ቀጠሉ ነው’’ ሲሉ እንደራሴው ተናግረዋል፡፡
‘’በአማራ ክልል ንጹሃን በድሮን እና በከባድ መሳሪያ እየሞቱ ነው’’ ሲሉ የምክር ቤት አባሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት የምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ አንስተዋል፡፡
‘’የሲቪል ተቋማትም እየወደሙ ነው’’ ሲሉ አስረድተዋል፡፡
‘’በአዲስ አበባ፣ በአማራ ክልል እና በተለያ አካባቢዎች አስር ቤቶች የተጨናነቁት ያለፍርድ በታጎሩት አማራዎች ነው’’ ሲሉም ተናግረዋል፡፡
የምክር ቤቱ አባል የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ የክልሉ ምክር ቤት አባላት ሆነ ተብሎ በሚመስል ሁኔታ ከአንድ ዓመት በላይ ያለፍርድ አሉ ብለዋል፡፡
‘’ጋዜጠኞች፣ አንቂዎች፣ ፖለቲከኞች ለሁለት ዓመት ያህል ያለ ፍርድ በእስር ቤቶች፣ አሉ ፍትህ የሚያገኙት መቼ ነው’’ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጠይቀዋል፡፡
‘’ዜጎች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው መስራት አልቻሉም መንገስት ይህን ችግር የሚፈታው መቼ ነው’’ የሚል ጥያቄም ተነስቷል።
‘’የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ምን አመጣ፣ የውጭ ምንዛሬ ግኝት ላይስ ምን ለውጥ አመጣ?’’ በሚልም እንደራሴዎች ጥያቄዎቻቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅርበዋል።
በቁጫ እና ዘይሴ ምርጫ ክልልሎች ህገመንግስታዊ ጥያቂ ያነሱ ሰዎች፣ የህዝብ ተወካዮች ላይ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈፀመ ነው፤ መንግሰት ያስቁም በሚልም እንደራሴዎች አንስተዋል።
ሌሎች ጥያቄዎችም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረቡ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩም መልስ መስጠት ጀምረዋል
ያሬድ እንዳሻው
Commentaires