top of page

ጥቅምት 21፣2016 - አሜሪካ በሐማስ ታግተው ወደ ጋዛ የተወሰዱ ታጋቾችን ለማስለቀቅ የሚረዱ የልዩ ሀይል ወታደሮችን ወደዚያው ልትልክ ነው ተባለ

ከወር ገደማ በፊት የፍልስጤማውያኑ የጦር ድርጅት /ሐማስ/ በእስራኤል ላይ ድንገት ደራሽ ጥቃት ሲያደርስ ከ200 በላይ ታጋቾችን ወደ ጋዛ መውሰዱ ሲነገር ሰንብቷል፡፡


ሐማስ ይዟቸው ከሰነበቱ ታጋቾች በሰብአዊ ርህራኔ በሚል ምክንያት የለቀቀው ጥቂቱን ብቻ ነው፡፡


እስራኤል በምድር ሀይል በከፈተችው ጥቃት ታጋቾቹንም የማስለቀቅ አላማም ያለው ነው ተብሏል፡፡


አሜሪካም ይሄን ግዳጅ የሚረዱ የልዩ ሀይል ወታደሮቿን ወደ ጋዛ እንደምትልክ ታይምስ ኦፍ እስራኤል ፅፏል፡፡


ይሁንና ምን ያህል የአሜሪካ ልዩ ሀይል ወታደሮች በዚህ ግዳጅ እንደሚሰለፉ የተጠቀሰ ነገር የለም፡፡

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page