ጥቅምት 20፣2017 - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ነገ በፓርላማ ቀርበው ማብራሪያ ሊሰጡ ነው
- sheger1021fm
- Oct 30, 2024
- 1 min read
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ነገ በፓርላማ ቀርበው ማብራሪያ ሊሰጡ ነው፡፡
ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀስላሴ በመስከረም ወር መጨረሻ ለህዝብ እንደራሴዎች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ባቀረቡት የመንግስትን ዕቅድ ላይ ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ያቀረቡትን እቅድ አስታከው የ #ፓርላማ አባላትም ለሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች ጭምር ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ማብራሪያ የሚሰጡት ተብሏል፡፡
ከፓርላማው ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው ነገ ምክር ቤቱ በሚያካሂደው መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች እና የአለም አቀፉ ተቋማት ተጠሪዎች እንዲሁም የሃይማኖት አባቶች ይገኛሉ፡፡
ትዕግስት ዘሪሁን
Comments