ጥቅምት 20፣2017 - አዋሽ ኢንሹራንስ በ 2016 በጀት ዓመት ከ 3.1 ቢሊዮን ብር በላይ አጠቃላይ የአረቦን ገቢ መሰብሰቡን ተናገረ፡፡
- sheger1021fm
- Oct 30, 2024
- 1 min read
ኩባንያው በበጀት ዓመቱ ከታክስ በፊት 902.6 ሚሊዮን ብር በላይ ዓመታዊ ጥቅል ትርፍ ማግኘቱንም ለሸገር ራዲዮ በላከው መግለጫ ተናግሯል፡፡
ይህም የትርፍ ዕድገት ከ64 በመቶ ከፍ ያለ ነው ተብሏል፡፡
#አዋሽ_ኢንሹራንስ በበጀት ዓመቱ ማጠቃለያ በአጠቃላይ ኢንሹራንስ ከ2.6 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን ጠቅሷል፡፡
በሕይወት ኢንሹራንስ ዘርፍ ደግሞ የ443.7 ሚሊዮን ብር #አረቦን ገቢ መሠብሰቡን ተናግሯል፡፡
በሁሉም የሥራ ዘርፎች የበጀት ዓመት የገቢ ዕድገት ከ28 በመቶ በላይ ነው ተብሏል፡፡
ኩባንያው በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ብቻ በተለያዩ ኩባንያዎች ከ387.9 ሚሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ #ኢንቨስትመንት በማድረግ በድምሩ የ1.25 ቢሊዮን ብር የአክሲዮን ባለድርሻ መሆን መቻሉን አስረድቷል፡፡

ለየኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ቦንድ በ 77.11 ሚሊዮን ብር፤ የልማት ባንክ ቦንድ ግዥ ከ76.3 ሚሊዮን ብር በላይ ግዥ መፈፀሙን ተናግሯል ፡፡
ኩባንያው ለበጀት ዓመቱ በሁሉም የኢንሹራንስ የሥራ ዘርፎች ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ የካሣ ክፍያ መክፈሉን ተጠቅሷል፡፡
የአዋሽ ኢንሹራንስ አጠቃላይ ሀብት ከ7.7 ቢሊዮን ብር፣ የተከፈለ ካፒታሉም ከ1.9 ቢሊዮን ብር፣ የተፈረመው ካፒታሉ ደግሞ 3.9 ቢሊዮን ብር መድረሱን ሰምተናል፡፡
ኩባንያው የ30ኛ ዓመት የምሥረታ ክብረ-በዓሉን በልዩ ልዩ መርሃ ግብሮች እያከበረ ነው፡፡
Comments