top of page

ጥቅምት 20፣2017 - በሞሪንጋ ወይም ሺፈራው ተክል በተለያዩ ጊዜያት በተደረገ ጥናትና ምርምር ከፍተኛ ፕሮቲን እንዳለው ይነገራል

  • sheger1021fm
  • Oct 30, 2024
  • 1 min read

በሞሪንጋ ወይም ሺፈራው ተክል በተለያዩ ጊዜያት በተደረገ ጥናትና ምርምር ከፍተኛ ፕሮቲን እንዳለው ይነገራል፡፡


የሞሪንጋ ወይም ሺፈራው ቅጠል በደቡቡ የኢትዮጵያ ክፍል አካባቢ ለምግብነት ሲውል ይታያል፡፡


ተክሉ ከምግብነት ባለፈ ለመድሃኒትነትም ጥቅም እንዳለው ከዚህ በፊት በተደረጉ ጥናቶች የተረጋገጠ ሲሆን አሁን ደግሞ አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ባደረገው ምርምር ለመቀንጨር ችግር ፍቱን መሆኑን ተረጋግጧል ተብሏል፡፡


ጥናቱን ያካሄደው አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሞሪንጋ ወይም ሺፈራው ተክል በተለያየ መንገድ አዘጋጅቶ ህፃናትን መመገብ የመቀንጨር ችግር እንደሚፈታ በጥናት መረጋገጡን ዩንቨርስቲው አስረድቷል፡፡


ጥናቱን ያካሄዱት በዩኒቨርስቲው ተመራማሪ የሆኑት አዲሱ ፍቃዱ(ዶ/ር) እንዳሉን ሞሪንጋን ከተለያዩ ምግቦች ጋር አቀነባብረን መመገብ ከፍተኛ ፕሮቲን እንድናገኝ ይረዳል፡፡


ኢትዮጵያ ውስጥ የህፃናት መቀንጨር በከፍተኛ ደረጃ እንዳለ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ማረጋገጡን የነገሩን ዶክተር አዲሱ ፍቃዱ ለዚህ ችግር ሞሪንጋ አንዱ መፍትሄ ሊሆን እንደሚችል በጥናቱ ተረጋግጧል ብለዋል፡፡


‘’አሁን ላይ የተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም በየትምህርት ቤቶች እየተካሄደ ነው፤ ለተማሪዎቹ በሚሆን መንገድ ተዘጋጅቶ ሞሪንጋ እንደ አንዱ የምግብ ግብአት ሆኖ ቢዘጋጅ መቀንጨርን ለመከላከል ይረዳናል’’ ሲሉ ያስረዳሉ፡፡


አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከደቡብ የኢትዮጵ ክልል እና ከአጋር አካላት ጋር በመሆኑ ሞሪንጋ ተክልን ቅጠልን አቀነባብሮ በፋብሪካ ለማዘጋጀት ስራዎች እየተጠናቀቀ መሆኑን ተመራማሪው ዶክተር አዲሱ ፍቃዱ ተናግረዋል፡፡


በፋብሪካ ደረጃ ሲዘጋጅ ተፈጥሯዊ ይዘቱ እንዳይለቅ ምን ዝግጅት ተደርጓል ብለን የጠየቅናቸው አዲሱ ፍቃዱ(ዶ/ር) ፋብሪካው እንዲተከል የተደረገው ተክሉ ያለበት ስፍራ ነው ከዚህም ባለፈ በየጊዜው የጥራት ክትትል እናደርጋለን ሲሉ መልሰዋል፡፡


ሞሪንጋን ወይም ሺፈራው ተክልን በፋብሪካ ደረጃ በሻይ ቅጠል፣ ዱቄት እና ለሾርባ ምቹ ተደርጎ ይዘጋጃል የተባለ ሲሆን ስራው በቅርብ ጊዜ አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑን ሰምተናል፡፡


ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ


በረከት አካሉ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page