top of page

ጥቅምት 2፣2017 - የጋራ ምክር ቤት ከምክክር ሂደቱ ራሳቸውን ያገለሉትን ወደ ንግግር እንዲገቡ የድርሻዬን እንድወጣ መንግስት እና የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጠይቀውኛል አለ

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ከምክክር ሂደቱ ራሳቸውን ያገለሉ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ሆኑ በትጥቅ ትግል ላይ ያሉ አካላት ወደ ንግግር እንዲገቡ የድርሻዬን እንድወጣ መንግስት እና የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጠይቀውኛል አለ፡፡


የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንም የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሁሉም አካላት ወደ ምክክር እንዲገቡ የድርሻውን እንዲወጣ መጠየቁን አረጋግጧል፡፡


የፖለቲካ ፓርዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ደስታ ዲንቃ ሀሙስ ዕለት ከምክክር ኮሚሽን ጋር በነበረን ወይይት ከተጠቀሱት አካላት ጋር ተያይዞ ወደ ምክክሩ ባለመግባታቸው ችግሮች መኖራቸውን ነግሮናል ብለዋል፡፡


ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች እና በትጥቅ ትግል ላይ ያሉ አካላት ካልተሳተፉ ወጤታማ የሆነ ምክክር ለማድረግ እንቅፋት ሊሆን እንደሚችል ኮሚሽኑ ነግሮኛል እኛ ሁሉን ያላካተተ ምክክር ውጤት እንደማያመጣ ለኮሚሽነሮቹ አስረድተናል ሲሉ ሰብሳቢ ተናግረዋል፡፡


አቶ ደስታ ከብልጽግና ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር ከሆኑት አቶ አደም ፋራ ጋርም በዚሁ ጉዳይ ላይ ሰሞኑን ተነጋግረናል ብለዋል፡፡





ያሬድ እንዳሻው

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page