top of page

ጥቅምት 2፣2017 - ዘመን ኢንሹራንስ በ2016 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት ብር 181.3 ሚሊዮን ብር አተረፍኩ አለ።

  • sheger1021fm
  • Oct 12, 2024
  • 1 min read

ኩባንያው በዛሬው እለት የባለአክሲዮኖች 6ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ማካሄዱን ለሸገር በላከው መግለጫ ተናግሯል።


#ዘመን ኢንሹራንስ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት 545.3 ሚሊዮን ብር የአረቦን ገቢ መሰብሰቡን ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ67.5 በመቶ ጭማሪ እንዳለው አስረድቷል።


በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ኩባንያው በአጠቃላይ 103.3 ሚሊዮን ብር ጠቅላላ የካሳ ክፍያ ከፍያለሁ ያለ ሲሆን፣ ለተሸከርካሪ ዋስትና የተከፈለው የካሣ መጠን ትልቁን ድርሻ ይዟል ብሏል፡፡


ኩባንያው ከመድን ውል ሥራ 166.2 ሚሊዮን ብር ውጤት አግኝቻለሁ ብሏል።


በጀት ዓመቱ ኩባንያው ከታክስ በፊት ብር 181.3 ሚሊዮን ትርፍ አስመዝግቧል፣ የ 74 በመቶ የትርፍ ድርሻ(Earning Per Share) ለባለአክስዮኖች አዳስገኘም ኩባንያው ለሸገር ነግሯል።


ዘመን ኢንሹራንስ ከተመሰረተ 4 ዓመት የሞላው ሲሆን፤ ጠቅላላ ሃብቱን 961.5 ሚሊዮን ብር ያ፤ የተከፈለ ካፒታሉ ደግሞ 234.2 ሚሊዮን ብር ደርሷል ተብሏል።

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page