ጥቅምት 2፣2017 - አክሲዮኖችንግዑዝ አልባ የማድረጊያ ረቂቂ መመሪያ ይፋ ማድረጉን የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ተናገረ
- sheger1021fm
- Oct 12, 2024
- 1 min read
ሰነደ ሙዓለ ንዋዮችን (አክሲዮኖችን) ግዑዝ አልባ የማድረጊያ ረቂቂ መመሪያ ይፋ ማድረጉን የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ተናገረ፡፡
መመሪያው ከመጽደቁ በፊት ህዝብ ውይይት እንደሚያደርግበት ተነግሯል፡፡
ከማህበረሰቡ በሚቀርቡ ሀሳቦች ረቂቁን ማዳበር እና ስራው ግልፅ የሆነ የአሰራር ሂደት እንደሚከተል ማሳየት የውይይቱ ዋና አለማ ነው ተብሏል፡፡
ሪቂቅ መመሪያው ላይ ግምገማ እና አስተያየት መስጠት ለሚፈልግ አካላት፤ በሩ ክፍት እንደሆነ ባለስልጣኑ ተናግሯል፡፡
ግምገማ እና አስተያየት የመስጫ ጊዜውም ከዛሬ ጥቅምት 2፣2016 ጀምሮ ለሁለት ሳምንታት የሚቆይ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡
ባለስልጣኑ፤ ህዝባዊ ውይይቱ ላይ መሳተፍም የሚፈልግ በዚህ አድራሻ (ecma.gov.et) ያሳውቀኝ ያለ ሲሆን በረቅቅ መመሪያው ላይ አስተያየት ለመስጠት ደግሞ (communications@ecma.gov.et) ተጠቀሙ ብሏል፡፡
ማንያዘዋል ጌታሁን
تعليقات