top of page

ጥቅምት 19፣2017 - ‘’ገሊላ ማንፋክቸሪንግ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር’’ ያስገነባውን የጫማ ማምረቻ ፋብሪካ አስመረቀ

  • sheger1021fm
  • Oct 29, 2024
  • 1 min read

በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ፤ ‘’ገሊላ ማንፋክቸሪንግ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር’’ ያስገነባውን የጫማ ማምረቻ ፋብሪካ አስመረቀ።


ፋብሪካው ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበት የተገነባ ሲሆን በቀን 2,000 የህፃናት እና የአዋቂ ጫማዎችን እንደሚያመርት ተነግሯል።

ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ስራ ሲጀምር በቀን 4,000 ጫማዎችን እንደሚያመርት ሰምተናል።


የገሊላ ማኑፋክቸሪንግ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ እና ባለቤት አቶ በርሄ አሰፋ ኩባንያው የተለያዩ አይነት ጫማዎችን እንደሚያምርት እና ምርቶቹንም ለሀገር ውስጥ ገበያ ከማቅረብ ባሻገር ወደ ተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት እንደሚልኩም ተናግረዋል።


ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ

ፍቅሩ አምባቸው

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page