ከህዳር 1 ጀምሮ ዲጂታል መታወቂያ ያለያዘ ወይም የተመዘገበበትን ማቅረብ ለማይችል ተገልጋይ አገግሎት አልሰጥም ሲል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ተናገረ፡፡
ነዋሪዎች አገልግሎቱን ለማግኘት ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ወይም የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረባቸው አስፈላጊ መሆኑ አምኜበታለሁ ብሏል ተቋሙ፡፡
ይህ ተግባራዊ ሚደረገው በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙት 16 ቅርንጫፎች መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

ተቋሙ ለሚሰጠው አገልግሎት ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ወይም የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ ግዴታ አድርጌዋለሁ ያለው ከሚቀጥለው ህዳር 1 ቀን 2017 ዓ ም ጀምሮ እንደሆነ በማህበራዊ የትስስር ገፁ ላይ ተናግሯል፡፡
በብሔራዊ ደረጃ ከሁለት ዓመት በኋላ 90 ሚሊዮን ሰዎች የዲጂታል መታወቂያ እንደሚኖራቸው እቅድ ተይዟል መባሉ አይዘነጋም።
Comments