top of page

ጥቅምት 19፣2017 - ‘’የህዝብ ጥያቄ ይዘን ወደ ሚኒስትሮች ቢሮ ስንሄድ እንድንገባ አይፈቀድልንም፣ የሉም እየተባልን እንቸገራለን’’ የህዝብ እንደራሴ

‘’የህዝብ ጥያቄ ይዘን ወደ ሚኒስትሮች ቢሮ ስንሄድ እንድንገባ አይፈቀድልንም፣ የሉም እየተባልን እንቸገራለን’’ ሲሉ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባል ተናገሩ፡፡


አንድ ተሿሚ፣ አመራር ከስልጣኑ ሲወርድ ህዝቡ ጋር እንደሚገባው፤ በሹመቱ ሰዓትም ህዝቡ ጋር መኖር እንዳለበትም የፓርላማ አባል አንስተዋል።


ይህ የተባለው 6ኛው የህዝብ እደራሴዎች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው።


በዚሁ ስብሰባ ላይም አንድ የፓርላማ አባል ‘’ተሿሚዎች በፓርላማው አባላት በኩል የሚታወቁትም ሆነ የሚታዩት ሹመት ለመቀበል ነው’’ ብለዋል።


እነኝሁ አባል አክለውም የፓርላማ አባላት የህዝብ ጥያቄ ይዘው ወደ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በሚሄዱበት ሰዓት ከጥበቃ እስከ ጸሐፊ ሚኒስትሮቹን እንዳያገኟቸው እንደሚከለክሏቸው እና ራሳቸው ሚኒስትሮቹም ጭምር ሊያስተናግዷቸው ፍቃደኛ አለመሆናቸውን ተናግረዋል።


የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትሩ በበኩላቸው ችግሩ አለ ፤ ይህም እንዲፈታ መንግስት በትኩረት እየሰራበት ነው ብለዋል፡፡


ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ


ፍቅሩ አምባቸው

Comments


bottom of page