ጥቅምት 19፣2017 - ባለፉት 12 ዓመታት የኢትዮጵያ አየር ትራፊክ ተቆጣጣሪ ባለሞያዎች በጥናት ላይ የተመሰረት የደመወዝ ማሻሻያ እንዳልተደረገላቸው ተናገሩ፡፡
- sheger1021fm
- Oct 29, 2024
- 1 min read
ባለፉት 12 ዓመታት የኢትዮጵያ አየር ትራፊክ ተቆጣጣሪ ባለሞያዎች በጥናት ላይ የተመሰረት የደመወዝ ማሻሻያ እንዳልተደረገላቸው ተናገሩ፡፡
ባለሞያዎቹ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረጉ ሀገር አቀፍና አለማቀፍ የአየር በረራዎችን ከመቆጣጠርና ሰላማዊ ከማድረግም ባለፈ የኢትዮጵያን ክልልን አልፈው የሚሄዱ በረራዎችንም ይከታተላሉ፡፡
‘’ #የደመወዝ፣ ጥቅማጥቅም እና ሌሎች ጥያቄዎች የኢትዮጵያ አየር ትራፊክ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች ማህበር ሳነሳው የነበረ ጥያቄ ቢሆንም ዛሬም ድረስ ምላሽ ያላገኘ ነው’’ ሲል ተናግሯል፡፡
የማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ ግሩምነህ መሰረት ‘’በቅርቡ የኢትዮጵያ ሲቪል አቬዬሽ ባለስልጣን በራሱ አቅም ከጥቅማጥቅም ጋር በተያያዘ የሚነሱ ችግሮች ለመፍታት ጥናት እያደረገ መሆኑን ሰምተናል’’ ያሉ ሲሆን ሌ’’ሎች ጥያቄዎች ግን ዛሬም ድረስ ምላሽ እያገኙ አይደለም’’ ብለዋል፡፡
‘’ከፍተኛ የሆነ በረራዎች በኢትዮጵያ አየር ክልል ውስጥ እየተስተናገደ ነው’’ የሚሉት አቶ ግሩምነህ በተለይም የሱዳን አየር ክልልን ይጠቀሙ የነበሩ አውሮፕላኖች አሁን ላይ የኢትዮጵያን አየር ክልል እየመረጡ በመሆኑን ያስረዳሉ፡፡
ስራው ከሌሎች ጎረቤት ሀገራት የበለጠ ቢሆንም #የኢትዮጵያ_አየር_ትራፊክ_ተቆጣጣሪ_ባለሞያዎች የሚከፈላቸው ደመወዝ ግን ከሌሎች ጎረቤት ሀገራት ጋር ሲነፃፀር እጅግ ያነሰ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሲቪል አቬዬሽን ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር አቶ መንግስቱ ንጉሴ የተነሳው የጥቅማጥቅም ጥያቄ ላለፉት ተከታታይ አመታት እየተነሳ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እነዚህ ችግሮች ለመፍታት እየሞከረ ነው ያሉ ሲሆን በተለይም የጥቅማጥቅሙ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ጥናት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚንስትር አለሙ ስሜ የኢትዮጵያ አየር ትራፊክ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች ያነሱት የደመወዝና ጥቅማጥቅም ጥያቄ የሚመለሰው የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የጀመረው የሪፎርም ስራ ሲጠናቀቅ ነው በማለት አስረድተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሲቪል አቬዬሽን ባለስልጣን ባለፈው በጀት አመት 1.4 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን ሰምተናል፡፡
በረከት አካሉ
Comments