ጥቅምት 19፣2017 - በኢትዮጵያ ከ3.3 በላይ የሀገር ውስጥ ተፈናቃየች እንዳሉ ተነግሯል
- sheger1021fm
- Oct 29, 2024
- 1 min read
በየጊዜው በሚከሰቱ ማንነትን መሠረት ያደረጉ የታጠቁ ቡድኖች ጥቃቶች፤ በመንግሥት እና በታጠቁ ቡድኖች መካከል በሚደረጉ ግጭቶች እና ዘላቂ ፖለቲካዊ እና አስተዳደራዊ መፍትሔ ባልተሰጠባቸው የወሰን ይገባኛል ጥያቄዎች ምክንያት በሚከሰት ግጭት እና ጦርነት ሰዎችን ከመኖሪያ ቀያቸው ማፈናቀላቸውን ቀጠለዋል ሲል ኢሰመኮ ተናገረ፡፡
በአፋር፣ አማራ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ሐረሪ፣ ኦሮሚያ፣ ትግራይ፣ ሶማሊ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልሎች ተፈናቅለው እርዳታ ጠባቂ የሆኑ በየመጠለያ ጣቢያው እና ከማኅበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው የሚኖሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች አንዳሉ ኮሚሽወጣው ሪፖርት አስረድቷል።
በኢትዮጵያ ከ3.3 በላይ የሀገር ውስጥ ተፈናቃየች እንዳሉም ተነግሯል፡፡
ከእነዚህ መካከልም 2.2 ሚሊዮን ገደማዎቹ በግጭት እና ጦርነት የተነሳ የተፈናቀሉ ናቸው ተብሏል፡፡
16 ከሞቶ የሚሆኑት በድርቅ፣ የተቀሩት ደግሞ በአየር ንብረት ለውጥ፣ በልማት እንዲሁም በሌሎች ምክንያቶች የተፈናቀሉ እንደሆኑ ተነግሯል፡፡
ከአጠቃላይ ከሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መካከልም 56 ከመቶ የሚሆኑት ከአንድ ዓመት በላይ በተራዘመ መፈናቀል የቆዩ እንደሆኑ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በሪፖርቱ አስነብቧል፡፡
ማርታ በቀለ
Comentarios