top of page

ጥቅምት 19፣2017 - ህፃናት ልጆች የትምህርት ጊዜአቸውን በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ እንዲያሳልፉ ይገደዳሉ መባሉን ሰምተናል

  • sheger1021fm
  • Oct 29, 2024
  • 1 min read

‘’በግጭት፣ በጦርነት፣ በተፈጥሮ አደጋ ዋነኛ ተፈናቃይ የሆኑት ሴቶች፣ ህፃናት እና አረጋዊያን አስፈላጊ ድጋፍም እየቀረበላቸው አይደለም’' ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን(ኢሰመኮ) ተናገረ፡፡


በዚህም እነዚህ ሰዎች ለተደራራቢ ችግር ተጋላጭ እንዳደረጋቸው፤ በኮሚሽኑ የሴቶች፣ ህጻናት፣ አካል ጉዳተኞች እና አረጋዊያን መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረሀዋሪያ ለሸገር ራዲዮ አስረድተዋል፡፡


ከነበሩበት ቀዩ ለቀው በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ ከገቡም በኃላ የተለያዩ የመብት ጥሰቶች እንደሚፈፀምባቸው ኢሰመኮ ጠቅሷል፡፡


ለወለዱ ሴቶች፣ ለአካል ጉዳተኛ፣ ለህፃናት እና ለአረጋዊያን የሚደረገው ድጋፍ እጅግ አነስተኛ ነው ሲልም ተናግሯል፡፡


ህፃናት ልጆች የትምህርት ጊዜአቸውን በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ እንዲያሳልፉ ይገደዳሉ መባሉንም ሰምተናል፡፡


ማርታ በቀለ



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page