top of page

ጥቅምት 18 2018 - ኢትዮጵያና ኤርትራ ወደ ውጥረት የገቡት በቀይ ባህር ጉዳይ መሆኑን ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ተናገሩ

  • sheger1021fm
  • Oct 28
  • 1 min read

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ከ20 ዓመታት ፀብ በኋላ መልሰው ሰላም ባወረዱ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ወደ ውጥረት የገቡት በቀይ ባህር ጉዳይ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ፡፡


ውጥረቱ ወደ አደባባይ የወጣው ግን የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ከተፈረመ በኋላ መሆኑንም አስታውሰዋል፡፡


ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት በእርቁ ሰሞን በሁለቱ ሃገራት መካከል ድንበሮች ተከፍተው፣ የአሰብን ወደብም ኢትዮጵያ ልትጠቀም ሂደት ተጀምሮ እንደነበር በማስታወስ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡ ከፓርላማ አባላት ለተነሳላቸው ጥያቄ በመሰጡት ምላሽ ነው፡፡


የቀይ ባህር ጉዳይ መልክአ ምድራዊ እና ታሪካዊ ጥያቄ በመሆኑ በሰከነ መንገድ ውይይት ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናግረዋል፡፡


ኢትዮጵያን የባህ በር ያሳጣትን ታሪካዊ ዳራ ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ህዝብ በሪፈንደም ያልተወሰነበት ፓርላማው የማያውቀው፣ የካቢኔ ውሳኔም ያልተላለፈበት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡


ኢትዮጵያ ቀይ ባህርን ያጣችበት አንድ ገፅ እንኳን ህጋዊ ሰነድ አልተገኘም ሲሉም ለፓርላማው አብራርተዋል፡፡


ቀይ ባህርን ለማጣት 30 ዓመት የወሰደ ትግል ኢትዮጵያ ውስጥ እንደነበርም አስታውሰው መልሶ ቀይ ባህርን ለማግኘት ግን ያን ያህል ዓመት ይወስድብና ብዬ አልገምትም ብለዋል፡፡


የኢትዮጵያ መንግስት ከማንም ጋር ውጊያ እንደማይፈልግ ለፓርላማው የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ውጊያ ከተጀመረ ግን ውጤቱ ግልፅ ነው የኢትዮጵያ አቅም አስተማማኝ ነው ብለዋል፡፡


ትዕግስት ዘሪሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page