ጥቅምት 18፣2017 - ከችሎት ላይ ጭምር እየተወሰዱ ታስረዋል ከተባሉ የአማራ ክልል ዳኞች መካከል ስድስቱ መፈታታቸው ተሰማ
- sheger1021fm
- Oct 28, 2024
- 1 min read
ህግ ተጥሶ ያለመከሰስ መብታቸው ሳይነሳ ከችሎት ላይ ጭምር እየተወሰዱ ታስረዋል ከተባሉ የአማራ ክልል ዳኞች መካከል ስድስቱ መፈታታቸው ተሰማ፡፡
የክልሉ ዳኞች ማህበር እንደተናገረው የዳኞች ያለመከሰስ መብት በአማራ ክልል ህጋዊ ከለላ እያገኘ አይደለም፡፡
በዚህም ምክንያት ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ ከ45 በላይ #ዳኞች ታስረው እንደነበር አስታውሷል፡፡
በቅርቡ በባህር ዳር ከተማ ታስረዋል ከተባሉ 13 ዳኞች መካከልም ከ10 ቀን እስር በኋላ 2 የከፍተኛ ፍርድ ቤት እና 2 የወረዳ ፍርድ ቤት ዳኞችን ጨምሮ 6 ዳኞች ከእስር መለቀቃቸውን ማህበሩ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ተናግሯል፡፡
留言