top of page

ጥቅምት 18፣2017 - ኢትዮጵያ ያላት የመሬት መንቀጥቀጥ መለኪያ መሳሪያ በቁጥርም 4 ብቻ ናቸው ተብሏል

  • sheger1021fm
  • Oct 28, 2024
  • 1 min read

በአዋሽ ፈንታሌ በርዕደ መሬት መለኪያ(Richter scale) በተለያያ ደረጃ የተመዘገበውን የመሬት መንቀጥቀጥ፤ በተለያዩ ማህበራዊ የትስስር ገጾች እንዳሻቸው የሚዘግቡ ግለሰቦች ህብረተሰቡን እያደነጋገሩት ነው ተባለ፡፡


በአዋሽ ፈንታሌ የመሬት ውስጥ ቅልጥ አለት ወደውጭ ቢገነፍል የከፋ ጉዳት ሊያስከትል ስለሚችል ጥንቃቄ ሊደርግ እንደሚገባ ተነግሯል፡፡


ኢትዮጵያ ያላት የመሬት መንቀጥቀጥ መለኪያ መሳሪያ በቁጥርም 4 ብቻ ናቸው ተብሏል፡፡


እነዚህም የመለኪያ መሳሪያዎችም በእርዳታ የተገኙ እንደሆኑ ከአታላይ አየለ(ፕ/ር) ሰምተናል፡፡


አታላይ አየለ(ፕ/ር) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ትምህርት ክፍል ሀላፊ እና የመሬት መንቀጥቀጥ ሳይንስ ተመራማሪና መምህር ናቸው፡፡


ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page