top of page

ጥቅምት 18፣2017 - በህገ-ወጥ መንገድ ከሀገራቸው የሚወጡ ስደተኞች ቁጥር ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ ነው ተባለ

በህገ-ወጥ መንገድ ከሀገራቸው የሚወጡ ስደተኞች ቁጥር ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ ነው ተባለ፡፡


18 ዓመት ያልሞላቸው ህፃናት ጭምር በህገወጥ መንገድ ከሀገር እንደሚወጡ ተነግሯል፡፡


ይህንን የተናገረው የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው፡፡


በዓመትም ከ150,000 እስከ 200,000 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ከሀገር ይወጣሉ የተባለ ሲሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ ፍልሰቱ ጨምሯል ይላሉ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የህገወጥ የሰዎች ዝውውር መከላከል እና የተመላሽ ዜጎች ክትትልና ድጋፍ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ደረጄ ተግይበሉ፡፡


በዚህም በህገወጥ መንገድ ከሀገር ወጥተው በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በኩል ከመጋቢት 2014 ዓ.ም እስከ መጋቢት 2015 ዓ.ም ባለው አንድ ዓመት ውስጥ ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ ከ130,000 በላይ ዜጎች ከ6,000 በላዩ 18 ዓመት ያልሞላቸው ህፃናት ናቸው መባሉን ሰምተናል፡፡


በህገወጥ መንገድ የሚደረግን ፍልሰት ለመቀነስ የሚከወኑ ስራዎች ቢኖርም ችግሩ ግን አሁንም መኖሩ በተደጋጋሚ የሚነሳ ነው፡፡


መንግስትም ህገወጥ ፍልሰትን ለመቆጣጠር ከጎረቤት ሀገራ ጋር ስራዎችን እየከወንኩ ነው ብሏል፡፡


ህገወጥ ደላሎችን ለህግ አሳልፎ አለመስጠት፣ ህገወጥ ፍልሰትን ማህበረሰቡ ማበረታታቱ፣ የግንዛቤ እጥረት እና ለሎችም ችግሮች ታክለውበት ህገወጥ ፍልሰቱ ላይ በሚሰራ ስራ ልክ ለውጥ እንዳመጣ አድርጎታል ተብሏል፡፡


በሌላ በኩል ደግሞ በችግር ውስጥ ያሉ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው የመመለስ ስራ እየተሰራ መሆኑን የተናገረው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተመላሾቹ ወደ ሀገር ቤት ከተመለሱ በኋላ ስራ የመስራት ፍላጎት ማጣት፣ ወደመጡበት ሀገር በድጋሚ መመለስ መፈለግ እና ሌሎችም ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሀገር ቤት በመመለሱ ሂደት ውስጥ የሚያጋጥሙ ችሮች ናቸው ብሏል፡፡


በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በኩል የሚከወነው ስራ ውሀ ቅዳ ውሀ መለስ እንዳሆን በህገወጥ መንገድ ተመልሰው የሚሄዱ እና አዲስ መንገደኞችን ለመቀነስ ስራዎችን እየከወኑ መሆኑን አቶ ደረጄ ተናግረዋል፡፡


ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ… https://tinyurl.com/2hyht637


ፋሲካ ሙሉወርቅ


コメント


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page