top of page

ጥቅምት 17፣2016 - ዘመን ባንክ እና ሳፋሪኮም ኤም ፔሳ አብረው ለመስራት ተስማሙ



የስምምነት የፊርማ ስነስርዓቱም በትናንትናው እለት በዘመን ባንክ ዋና መስሪያቤት ተከናውኗል።


የስምምነት ፊርማውን የዘመን ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ደረጀ ዘነበና የሳፋሪኮም ኤምፔሳ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፖል ካቫቩ ተፈራርመውታል።


ስምምነቱ ዘመን ባንክ የሳፋሪኮም ኤምፔሳ ከፍተኛ ወኪል (ሱፐር ኤጀንት) በመሆን የሞባይል ባንኪንግ ስራዎችን በቀለጠፈ መንገድ መስጠት ያስችላል ተብሏል።


በስምምነቱ መሰረት የዘመን ባንክ ደንበኞች ገንዘብ ወደ ኤምፔሳ ፣ ከኤምፔሳ ሂሳባቸው ወደ ዘመን ባንክ ሂሳባቸው ማስተላለፍ እንዲችሉ፣ የአገልግሎት ክፍያዎችን እንዲከፍሉ፣ የሂሳብ መረጃዎችን እንዲያዩ፣ የአየር ሰዓት እንዲገዙ እና ሌሎችንም የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎቶች እንዲያገኙ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡


የሳፋሪኮም ስልክ ቁጥር ያላቸው የዘመን ባንክ ደንበኞች ወደ ባንኩ ቅርንጫፎች ጎራ በማለት አገልግሎቱን እንዲያገኙ ማስደረግ ይችላሉ ተብሏል።


ዘመን ባንክ ከዘመኑ ጋር የዘመኑ የባንክ አገልግሎቶችን በመስጠት ቀዳሚ ባንክ መሆኑን የተናገሩት የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ደረጀ ዘበነ ወደፊትም አዳዲስ ፈጠራዎች የታከሉበት፣ ደንበኞቹን የሚመቹ የዲጂታል የባንክ አገልግሎትን በስፋት መስጠቱን ይቀጥልበታል ብለዋል።


ዘመን ባንክ የተፈረመ ካፒታሉ 14 ቢሊዮን ብር፣ የተከፈለ ካፒታሉ ደግሞ 5.7 ቢሊዮን ብር መሆኑን ተናግሯል ።

የባንኩ ቅርንጫፎች ብዛት 110 እንደሆኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጠቅሰዋል።


ከወራት በፊት የሞባይል የገንዘብ አገልግሎት እንዲሰጥ ከብሔራዊ ባንክ ፍቃድ እንደተሰጠው የተናገረው ኤም-ፔሳ ከኬንያ በተጨማሪ በሌሎች አገሮች የሚሰራ ሲሆን ኢትዮጵያ ስምንተኛ መዳረሻው ነች፡፡


ኩባንያ ከዘመን ባንክ ጋር እዳደረገው ዓይነት መሰል ስምምነት ከህብረት እና ከዓባይ ባንኮች ጋር ማድረጉ ይታወሳል።


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

Comments


bottom of page