ጥቅምት 16፣2017 - የአዲስ አበባን የነዋሪነት አገልግሎት ለማግኘት መሸኛቸውን ይዘው የሚጠባበቁ ሰዎች ብዛት 39,000 ደርሷል፡፡
- sheger1021fm
- Oct 26, 2024
- 1 min read
በአዲስ አበባ ሁሉንም የነዋሪነት አገልግሎት ለማግኘት በቅድሚያ የብሔራዊ ዲጂታል(ፋይዳ) መመዝገብ ግዴታ እንደሆነ ከአዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲው ሰምተናል፡፡
ከተለያዩ አካባቢዎች መልቀቂያ ይዘው የአዲስ አበባ የነዋሪነት አገልግሎት ለማግኘት ከዚህ ቀደም 6 ወር የሚጠብቁ የነበረ ሲሆን አሁን 3 ወር እንደሚጠብቁም ተነግሯል፡፡
ተገልጋዮች ወደ ኤጀንሲው ሲመጡ የተቀመጠውን መስፈርት ባለሟሟላታቸው መልቀቅያ ወይንም መሸኛ አምጥተው እንደሚጠብቁ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ነግረውናል፡፡
ከነዚህ ውስጥ የተቀመጠውን የ3 ወር ጊዜ የማይጠብቁ እና አስቸኳይ የሆነ ምላሽ የሚሰጣቸውም እንዳሉ አስረድተዋል፡፡
Comments