top of page

ጥቅምት 16፣2017 - ኖህ ሪል ስቴት በጥራት የሰራቸውን ከ650 በላይ የመኖሪያ አፓርታማዎችን እና የንግድ ቤቶችን አስረከበ

  • sheger1021fm
  • Oct 26, 2024
  • 2 min read

ኖህ ሪል ስቴት በጥራት የሰራቸውን ከ650 በላይ የመኖሪያ አፓርታማዎችን እና የንግድ ቤቶችን አስረከበ፡፡


መኖሪያ ቤቶቹ እና የንድድ ቤቶቹ የተገነቡት ኩባንያው "ኖህ ኤርፖርት ድራይቭ ሳይት" ሲል በጠራውና በሰሚት አካባቢ በሚገኘው መኖሪያ መንደር ነው፡፡


ዛሬ ለቤት ባለቤቶች የተላፉት መኖሪያ ቤቶች ከ75 ካሬ እስከ 128 ካሬ ስፋት ያላቸው መሆናቸው በቤት ማስረከቢያ ስነ ስርዓቱ ላይ ተነግሯል፡፡


ቤቶቹ ከባለ 2 እስከ ባለ 3 መኝታ ክፍሎች ያሏቸው ከ650 በላይ አፓርታማ የመኖሪያ ቤቶች፣ 32 በላይ ቪላ ቤቶች እና 45 የንግድ ሱቆች ናቸው፡፡


ኖህ ሪልስቴት ዛሬ ያስረከባቸው መኖሪያ ቤቶች መዋኛ ገንዳ፣ የከርሰምድር ውሃ እንዲሁም የስፖርት ማዝወተሪያን ያካተቱ መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡


የኖህ ሪል ስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፍቃዱ አዋሽ ‘’ኖህ ሪል ስቴት የመኖሪያ አፓርታማዎችን በጊዜ እና በጥራት በመገንባትና በማጠናቀቅ ኩባንያው የደንበኞቹን እምነት ያተረፈ ኩባንያ ነው’’ ብለዋል።


ኩባንያው በቅርቡ በእንቁላል ፋብሪካ "ኖህ አስኳልን" 750 በላይ መኖሪያ ቤቶችን፣ በአዋሬ ሴቶች አደባባይ "ኖህ ቪክትሪ ሳይት" 152 ቤቶችን ለቤት ባለቤቶች አንደሚያስረክብ አስረድቷል፡፡


ከዚሁ ጋር በተያያዘ ኖህ ሪል ስቴት በቀጣይ ወር በቦሌ ክ/ከተማ በተለምዶ ቦሌ ሆምስ በሚባለው አካባቢ ከ2500 በላይ የሚሆኑ ቤቶችን ግንባታ አስጀምራልሁ ብሏል፡፡

"ድርጅታችን እንደ ከዚህ ቀደም ህንፃዎችን በፍጥነት መገንባት ብቻ ሳይሆን ዘመናዊ የግንባታ ቡድን በማዘጋጀት፣ ዘመናዊ የኮንክሪት ማቀነባበሪያ መጠቀምን፣ ለድርጅታችን ትልቅ የኮንስትራክሽን የጥራት ላቦራቶሪ በማቋቋም ለምንገነባቸው ህንፃዎች በጥራት ከፍተኛ ቦታ የሚሰጥ ፤ ብሎም በ2015 ዓ.ም ያስጀመርነውን ዘመናዊ የበር እና የቁም ሳጥን ማምረቻ ትልቅ አቅም የሚፈጥር ይሆናል’’ ሲሉ የድርጅቱ መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ ቴዎድሮስ ዘሪሁን ተናግረዋል፡፡


ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለውም ‘’ኖህ ሪል ስቴት በተለይም ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ በቤት ልማት መጠነ ሰፊ ስራ ለመስራት የተነሳበት ወቅት ሲሆን የ5 ዓመት ስትራቴጂ እቅድ በመንደፍ ዘመናዊ የመኖሪያ መንደሮች ላይ ትኩረት በማድረግ ከተማችን ላይ በመኖሪያ ቤት አቅርቦት ላይ ሰፊ ስራዎችን ለመስራትና የከተማችንን አዲስ አበባን ውበት በሚመጥን መልኩ እስከ 2020 ዓ.ም አብዛኛውን የከተማችን ነዋሪዎች ተደራሽ የሚያደርጉና ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው ቤቶችን ገንብቶ ለማስረከብ እየሰራን ነው’’ ብለዋል፡፡


ኖህ ሪል ስቴት ባለፉት አስርት ዓመታት በ33 ሳይቶች ከ9,800 በላይ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የመኖሪያ ቤቶችን፣ የንግድ ማዕከላትን ለቤት ፈላጊዎች ገንብቶ አስረክቧል።


ድርጅቱ ‘’ፈጣን እና ቀልጣፋ በሆነ መልኩ ገንብቶ ያስረከባቸው መኖሪያ ቤቶች ለቤት ፈላጊዎች የዘመነ የመኖሪ ቤት፣ ለከተማችን ደግሞ ውብ መንደር ማሳያ ሆነዋል’’ ሲል ተናግሯል።


ንጋቱ ሙሉ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page