top of page

ጥቅምት 16፣2017 - በግጭት ውስጥ በቆዩ አካባቢዎች የወደሙ ጤና ተቋማት በበቂ ሁኔታ መልሰው ስላልተቋቋሙ የሚሞቱ እናቶች እና ህፃናት ቁጥር እየጨመረ ነው ተባለ፡፡

  • sheger1021fm
  • Oct 26, 2024
  • 1 min read

በግጭት ውስጥ በቆዩ አካባቢዎች የወደሙ ጤና ተቋማት በበቂ ሁኔታ መልሰው ስላልተቋቋሙ የሚሞቱ እናቶች እና ህፃናት ቁጥር እየጨመረ ነው ተባለ፡፡


በአንዳንድ ክልሎች የሚጣሉ ህፃናት ቁጥርም እንዲሁ ጨምሯል ተብሏል፡፡


የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በእናቶችና ሕፃናት ሰብአዊ መብት አያያዝ ላይ ለ1 ዓመት ያደረገውን ክትትልና ምርመራ ውጤት በሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡


በሪፖርቱ ከተጠቀሱት መካከል የሚከተሉት ነጥቦች ይገኙበታል፡፡


በግጭት ምክንያት የወደሙ የህክምና ተቋማት በበቂ መልሰው ስላልተቋቋሙ እናቶች የወላድ አገልግሎት ለማግኘት ተቸግረዋል፡፡


በአፋር፣ በአማራና በኦሮሚያ ክልል የሚጣሉ ህፃናት ቁጥር ጨምሯል፡፡


በህፃናት ማሳደጊያዎች ውስጥ በህፃናት ላይ የሚደርሰው የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዲስተካከል የተሰጡ ምክረ ሀሳቦች እየተተገበሩ አይደለም፡፡


በአዲስ አበባ በተለያየ ወንጀል ተሳትፈዋል የተባሉ ህፃናት በሚገቡበት የተሃድሶ ማዕከል የሰብአዊ መብት ጥሰት ይደርስባቸዋል፡፡




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page