በልማት የሚነሱ ሰዎች የሚተዋቸው ውሾች፤ በአዲስ አበባ ባለቤት አልባ ውሾች እንዲጨምሩ አድርጓል ተብሏል፡፡
በአዲስ አበባ በኮሪደር እና በሌሎችም ልማቶች ሳቢያ ከአካባቢያቸው የሚነሱ ሰዎች የተዋቸው ውሾች፤ ከባለቤት አልባዎቹ የጎዳና ውሾች ጋር እየተቀላቀሉ የባለቤት አልባ ውሾች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ተነግሯል፡፡
በከተማዋ እየበዙ መጥተዋል የተባሉት እነዚህ ባለቤት አልባ ውሾች፤ የእብድ ውሻ በሽታ ወደ ሰዎች እንዳያሰራጩ ስጋት ፈጥረዋል ተብሏል፡፡
ይህንን ያለው የአዲስ አበባ አርሶ አደር እና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ነው፡፡
ኮሚሽኑ ባለቤት አልባ ውሾቹ፤ የእብድ ውሻ በሽታ እንዳያሰራጩ ከጀርመን ድንበር የለሽ የሀኪሞች ማህበር ጋር በመሆን የክትባት ስራ እየከወነ እንደሆነም አስረድቷል፡፡
በዚህም በአራት ክፍለ ከተሞች 16,000 ውሾችን ለመከተብ እየተሰራ መሆኑንም ሰምተናል፡፡
በአሁን ሰዓት በከተማዋ የሚገኙ ባለቤት አልባ ውሾች ቁጥራቸው ስንት እንደሆነ ለማወቅ ተቸግሬአለሁም ብሏልየአዲስ አበባ አርሶ አደር እና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን፡፡
ወደፊት የውሾች ማቆያ እንዲኖር እና ተንከባካቢዎች የውሾቹን ጤና በመጠበቅና ውሾችን በመሸጥ የስራ እድል እንዲፈጠር ለማድረግ ታቅዷል ተብሏል፡፡
ወንድሙ ሀይሉ
Comentários