ከገበታ የአትክልት ምግቦች እንዳይጠፉ እንዲሁም ልዩ የጉርሻ ባህል እንዲበረታ ያግዛል የተባለ ዘመቻ ተጀመረ።
ፕሮግራሙን የጀመረው ''ክኖር'' ሲሆን ስያሜውንም “ምርጡ ጉርሻ” ሲል ሰይሞታል።
ይህ ዘመቻ ይፋ ከመደረጉ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ በኢትዮጵያዊያን የአመጋገብ ስርዓት ውስጥ የአትክልት ምግቦችን ጠቀሜታ ለማስተዋወቅ ያለመ ዝግጅት መደረጉ ተሰምቷል።
በኢትዮጵያ 39 በመቶ የሚሆኑት ከአምስት ዓመት በታች ያሉ ህጻናት የመቀንጨር ችግር የሚያጋጥማቸው ሲሆን፤ ይህም ሥር በሰደደ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት የሚመጣ መሆኑን የክኖር አምራች ኩባንያ ''ዩኒሊቨር'' ጥናቶችን ጠቅሶ አስረድቷል።
የምርጡ ጉርሻ ዓላማ ኢትዮጵያዊያን ጣፋጭ የአትክልት ምግቦችን አብስለው እንዲመገቡ እና ለወዳጆቻቸው የአትክልት ምግብን በጉርሻ እንዲጋብዙ በማነሳሳት እና ውጤታማ ለውጥ በማምጣት በህብረተሰቡ ውስጥ ተጨባጭ ልዩነት ለመፍጠር ያለመ ነው ተብሏል።
![](https://static.wixstatic.com/media/b24dd6_47bdfe7dc9a9467cb0b7ff207e92d86e~mv2.jpg/v1/fill/w_720,h_960,al_c,q_85,enc_auto/b24dd6_47bdfe7dc9a9467cb0b7ff207e92d86e~mv2.jpg)
የዩኒሊቨር አፍሪካ ኒውትሪሽን ፕላትፎርም ዳይሬክተር ሰላመክርስቶስ በላይ ''ምርጡ ጉርሻ ዘመቻ፤ የአትክልት ምግቦችን የኢትዮጵያውያን ገበታ አካል ለማድረግ እና የተሻለ የአመጋገብ ባህልን አብሮ በመብላት ውስጥ ከፍ ለማድረግ ያለመ ነው'' ብለዋል።
ክኖር ንቅናቄውን ለመምራት ከኮሜዲያን እሸቱ መለሰ ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑንም አስረድቷል።
ፕሮግራሙ ይፋ በተደረገበት ስነ-ሥርዓት ታዳሚዎች የአትክልት ምግቦችን ሲጎራረሱ ታይተዋል።
የክኖር አምራቹ ዩኒሊቨር በዓለም ዙርያ በ190 ሀገራት ውስጥ የሚሰራ ሲሆን የንጽሕና መጠበቂያዎች እና ምግቦችን የሚያመርት ኩባንያ ነው፡፡
ከተመሰረተ ከ130 ዓመታት በላይ ያስቆጠረው ዩኒሊቨር በ2007 ዓ.ም በኢትዮጵያ ቢሮው ከፍቶ በኢስተርን ኢንዱስትሪ ዞን የማምረቻ ፋብሪካውን ተክሏል።
ላይፍቦይ ሳሙና፣ ኦሞ፣ ክኖር አንኳር፣ ሰንላይት ሳሙናና የዱቄት ሳሙና እንዲሁም ሲግናል የጥርስ ሳሙና ያሉ የዩኒሊቨር ምርቶችን ናቸው፡፡
ንጋቱ ሙሉ
Comments