በ2017 የትምህርት ዘመን ወደ ዩኒቨርሲቲ ለሚቀላቀሉ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ፡፡
በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ወስደው ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ መደበኛ ተማሪዎች ፤ የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡
ተማሪዎች የተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ እነዚህ አድራሻዎችን በመጠቀም መመልከት ይችላሉ ተብሏል፡፡
በቀጣይም ተቋማቱ በሚያሳውቁት ቀን መሰረት ተማሪዎች ምዝገባ እንዲያከናውኑም ጠቁሟል፡፡
የዩኒቨርሲቲ ይቀየርልኝ ጥያቄ አላስተናግድም ሲልም ትምህርት ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡
በ2016 የትምህርት ዘመን፣ 12ኛ ክፍል ከተፈተኑ ተማሪዎች መካከል 94.6 በመቶዎቹ የማለፊያ ነጥብ አላስመዘገቡም መባሉ ይታወሳል፡፡
Comments