top of page

ጥቅምት 13፣2017 - የፒያሳ መልሶ ማልማት አካል በሆነው በ9.5 ሄክታር መሬት ላይ ግዙፍ የንግድ ሞሎችን እና የመኖሪያ ቤት ሊገነባ ነው፡፡

የፒያሳ መልሶ ማልማት አካል በሆነው በ9.5 ሄክታር መሬት ላይ ግዙፍ የንግድ ሞሎችን እና የመኖሪያ ቤት ሊገነባ ነው፡፡


ግንባታውን በ6 ወራት ውስጥ ገንብቶ ለማጠናቀቅ ስምምነት ላይ ተደርሷል።


የንግድ ማዕከላቱን እና የመኖሪያ ቤቱን የሚያስገነበው፤ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ሲሆን ገንቢው ደግሞ ኦቪድ ግሩፕ ነው፡፡

በስምምነቱ፤ የወርቅ ቤቶች፣ የንግድ ሱቅ ሞል፣ መዝቦልድ ሞል እና ጣይቱ የመኖሪያ አፓርትመንት በአልሙኒየም ፎርም ወርክ ቴክኖሎጂ በ6 ወራት ጊዜ ውስጥ ገንብቶ ወደ አገልግሎት ለማስገባት የሚያስችል ነው፡፡


ግንባታውን በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ሥራ መጠናቀቁም ተነግሯል።


በተጨማሪም ዘመናዊ የመኖሪያ ቤትም በዚሁ ስፍራ እንደሚገነባ ተጠቅሷል፡፡

ሳይቶችን በ6 ወራት ለማጠናቀቅ የሚያስችለው የአልሙኒየም ፎርምወርክ ቴክኖሎጂም ለግንባታ ዝግጁ ማድረጋቸውን ኦቪድ ተናግሯል፡፡


ሞሎቹ እና የመኖሪያ ቤቶቹ የሚገነቡት በፒያሳ መልሶ ማልማት ለልማት ዝግጁ በሆኑት የኮርፖሬሽኑ ይዞታዎች ላይ ነው ተብሏል፡፡


ንጋቱ ሙሉ

Comments


bottom of page