top of page

ጥቅምት 13፣2017 - ኤስኦኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ የ50ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አከበረ

  • sheger1021fm
  • Oct 23, 2024
  • 1 min read

ኤስኦኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ የ50ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አከበረ።


ኤስኦኤስ የህጻናት መንደሮች(sos children village) በኢትዮጵያ ከተመሰረተበት1966 ዓ.ም ጀምሮ በህጻናት፣ ቤተሰቦቻቸውና በማህበረሰብ የሚሰራ የልማት ድርጅት ነው።


ድርጅቱ በ50 ዓመታት ጉዞው በአጠቃላይ 8.1 ሚሊዮን ሰዎች በተለያዩ አገልግሎቶቹ መጥቀሙን ተናግሯል።


የእለት ደራሽ ድጋፍ ማቅረብ፣ የወጣቶች አቅም ግንባታና ጤና ድርጅቱ ከሚሰራቸው ስራቸው መካከል ይገኙበታል።


ኤስኦኤስ የህፃናት መንደር በ 50 ዓመት ውስጥ 100,000 ህፃናት ትምህርት እና ስልጠና አግኝተው ራሳቸውን እንዲችሉ አስረድቷል።


ድርጅቱ በአሁኑ ሰዓትም 495,000 በላይ ሰዎች በተለያዩ ፕሮግራሞች አገልግሎት እየሰጠሁ ነው ብሏል።


ኤስኦኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ ላለፉት አምስት አስርት ዓመታት ያስመዘገባቸውን ታላላቅ ስኬቶች በመዘከር ሲያካሄድ የነበረውን የምስረታ 50ኛ ዓመት ክብረ በዓል አጠናቋል።





ፍቅሩ አምባቸው

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page