top of page

ጥቅምት 12፣2016 - 6 ምዕራባዊያን ሀገሮች እስራኤል በጋዛ ሰርጥ የምትፈፅመውን ድብደባ በመደገፍ የጋራ መግለጫ ማውጣታቸው ተሰማ

የእስራኤልን የጋዛ ዘመቻ በመደገፍ የጋራ መግለጫ ያወጡት አሜሪካ ፣ ብሪታንያ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣሊያን እና ካናዳ እንደሆኑ አናዶሉ ፅፏል፡፡


ሀገሮቹ በጋራ መግለጫው የእስራኤልን የጋዛ የጦር ዘመቻ ራስን የመከላከል መብት ነው ማለታቸው ተሰምቷል፡፡


ሀገሮቹ የጋራ መግለጫውን ያወጡት በመሪዎች ደረጃ ምክክር ካደረጉ በኋላ መሆኑ ታውቋል፡፡


ሐማስ ወደ እስራኤል በመዝለቅ ድንገት ደራሽ ጥቃት ካደረሰ ወዲህ እስራኤል ያለ ፋታ ጋዛን እየቀጠቀጠችው ነው፡፡


ሰብአዊ ቀውሱም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ ነው ተብሏል

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

Comentarios


bottom of page