የዓለም የጉዞ ሸላሚ ድርጅት (ዎርልድ ትራቭል አዋርድ) በአፍሪካ ግዙፉ ለሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ 4 እውቅናዎችን እንደሰጠው ተሰማ።
የዓለም የጉዞ ሸላሚው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካ መሪ አየር መንገድ የሚለውን ሥያሜም እውቅና ሰጥቷል።
በዱባይ፣ በአፍሪካና በህንድ ውቅያኖስ አካባቢዎች በተካሄደው የ2023 የዓለም የጉዞ ሽልማት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካ መሪ አየር መንገድ እውቅና ባለፈ ተጨማሪ 3 ዕውቅናዎችን ማግኘቱን ነው የተነገረው።
አየር መንገዱ ዘንድሮ ዕውቅና ተሰጥቶታል።
ሸላሚ ድርጅቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድን በ’’ቢዝነስ ክላስ’’ ምርጥ አየር መንገድ እንዲሁም በሞባይል መተግበሪያም ቀላልና ምቹ አየር መንገድ የሚል ዕውቅና እንደሰጠው ከድርጅቱ ድረ ገፅ አንብበናል።
በአፍሪካ ስመ ጥር አየር መንገድም ዘርፍ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፊት እንደሆነ የሚያስረዳ እውቅና ተሰጥቶታል።
ሽልማት ሰጪው በጉዞ፣ በቱሪዝም እና በእንግዳ ተቀባይነት ኢንዱስትሪዎች ውስጥ በአገልግሎት የተመረጡትን በመምረጥ ይታወቃል።
ሸገር የመረጃውን ትክክለኛነት ከየኢትዮጵያ አየር መንገድ አረጋግጧል፡፡
ተህቦ ንጉሴ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
Comments