top of page

ጥቅምት 11 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች

  • sheger1021fm
  • Oct 21
  • 2 min read

የፈረንሳይ ሹሞች እጅግ ውድ የአገራችንን ቅርሶች ማስጠበቅ ተስኖናል ሲሉ በፀፀት ተናገሩ፡፡


የሹሞቹ አስተያየት የተሰማው በርዕሰ ከተማዋ ፓሪስ ከሚገኘው የሉቨር ቤተ መዘክር ውድ ጌጣ ጌጦች ከተሰረቁ በኋላ እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡


ጌጣ ጌጦቹ የአገሪቱ ቅርሶችም በመሆናቸው በዋጋ እንደማይታመኑ እየተነገረ ነው፡፡

ree

ከተዘረፉት ቅርሶች መካከል የፈረንሳዩ ንጉሰ ነገስት ናፖሊዮን በናፖርት ለባለቤቱ አበርክቶለት የነበረ በአልማዝ የተንቆጠቆጠ ሐብልም ይገኝበታል ተብሏል፡፡


ዘራፊዎቹ ላይ በፍጥነት ካልተደረሰባቸው ቅርሶቹን በማወላለቅ በትንሽ በትንሹ ወደ ውጭ አገራት ሊያሸሿቸው ይችላሉ የሚል ስጋት አሳድሯል፡፡


የፓሪሱ ዘረፋ በመሰል ቤተ መዘክሮች የደህንነት ጥበቃው በእጅጉ እንዲጠናከር የማንቂያ ደወል ሆኗል ተብሏል፡፡


የቤተ መዘክሩ የቅርሶች ዘረፋ በአገሪቱ ከፍተኛ ድንጋጤን እንደፈጠረ መረጃው አስታውሷል፡፡



የሱዳኑ ካርቱም አለም አቀፍ ኤርፖርት ዳግም ወደ አገልግሎት ሊመለስ ነው፡፡


ኤርፖርቱ በጦርነቱ ምክንያት ለ2 አመት ከመንፈቅ ጊዜ ተዘግቶ እና አገልግሎት አቋርጦ መቆየቱን አናዶሉ አስታውሷል፡፡


ኤርፖርቱ ከነገ አንስቶ በአገር ውስጥ በረራ ብቻ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር የአገሪቱ የሲቪል አቪየሽን ሹሞ ተናግረዋል፡፡


የሱዳን ጦር ካርቱምን ምን ከRSF ታጣቂዎች በመንጠቅ መልሶ ከተቆጣጠራት ከመንፈቅ በላይ ሆኖታል፡፡


የሱዳን መንግስት አስተዳደራዊ ማዕከሉን ወደ ካርቱም የመመለስ እቅድ አለው ተብሏል፡፡


የሱዳን መንግስት በጦርነቱ ምክንያት አስተዳደራዊ ማዕከሉን ወደ ወደብ ከተማዋ ፖርት ሱዳን ካዞረ መቆየቱን መረጃው አስታውሷል፡፡



የማዳጋስካሩ ወታደራዊ መንግስት መሪ ኮሎኔል ሚካኤል ራንዲያኒሪና አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሾሙ፡፡


በወታደራዊ ርዕሰ ብሔሩ በጠቅላይ ሚኒስትርነት የተሾሙት ሒሪንት ሳላማ ራጃኦ ናሪቬሎ እንደሆኑ አናዶሉ ፅፏል፡፡


ኮሎኔሉ በአገሪቱ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ተፈቅዶላቸው የአገሪቱ ጊዜያዊ ፕሬዘዳንት የተሰኝተው ቃለ መሐላ የፈፀሙት ባለፈው ሳምንት አርብ እለት ነው፡፡


መንግስታቸው የተገለበጠው የቀድሞው ፕሬዘዳንት አንድሬይ ራጆሊና ከግልበጣው አስቀድሞ ወደ ፈረንሳይ ኮብልለዋል ተብሏል፡፡


በማዳጋስካር የመንግስት ግልበጣ የተደረገው አገሪቱ ከ2 ሳምንታት በላይ ባስቆጠረ ህዝባዊ አመፅ ስትናጥ ከሰነበተች በኋላ ነው፡፡


ኮሎኔሉ ጊዜያዊ ርዕሰ ብሄር እንዲሆኑ የፈቀደው የአገሪቱ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት በ60 ቀናት ውስጥ ምርጫ እንዲጠሩ መጠየቁን መረጃው አስታውሷል፡፡



የኮሎምቢያ መንግስት በአሜሪካ የቆዩ አምባሳደሩን ወደ አገር ቤት አስጠራቸው፡፡


የደቡብ አሜሪካዊቱ አገር የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በዋሽንግተን ያስጠራቸው አገሪቱ ከአሜሪካ ጋር ያላት ግንኙነት በእጅጉ በደፈረሰበት ወቅት እንደሆነ አልጀዚራ ፅፏል፡፡


የአሜሪካው ፕሬዘዳንት የኮሎምቢያ መንግስት የአደገኛ ዕፅ ምርት እና ዝውውርን በወጉ መቆጣጠር ባለመቻሉ ከእንግዲህ ለአገሪቱ ሰባራ ሳንቲም በእርዳታ አልሰጥም ያሉት ሰሞኑን ነው፡፡


በዚያ ላይ ትራምፕ የኮሎምቢያውን ፕሬዘዳንት ራሱም የአደገኛ ዕፅ አስተላላፊዎቹ አለቃ ነው ሲሉ ዘልፈዋቸዋል ተብሏል፡፡


የኮሎምቢያው ፕሬዘዳንት ጉስታቮ ፔትሮ አሜሪካ በካሪቢያን ባህር በዘፈቀደ ታደርሳለች ያሉትን ጥቃት በግላጭ የተቃወሙት ቀደም ብሎ ነው፡፡


የአሜሪካ ጦር ጀልባዎቹን የመታሁት አደገኛ እፅ ጭነው ወደ አሜሪካ ሲያመሩ ነው ይላል፡፡


ጉስታቮ ፔትሮ ግን በድብደባው የተገደሉት ብዙዎቹ አሳ አስጋሪዎች ናቸው በሚል እየተሟገቱ ነው፡፡


አሜሪካ በዚህ ጉዳት ከቬኒዙዌላም ጋር ከባድ ውዝግብ ውስጥ እንደሆነች መረጃው አስታውሷል፡፡


የኔነህ ከበደ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page