ጥቅምት 11 2018 - በዓለም ዙሪያ በየቀኑ ከ100,000 በላይ የአየር በረራ እንደሚደረግ ይነገራል።
- sheger1021fm
- Oct 21
- 1 min read
በኢትዮጵያም በቀን የሚነሳና የሚያርፈው እንዲሁም በኢትዮጵያ የአየር ክልል የሚተላለፈው በረራ ከ600 በላይ ደርሷል።
ከዚህ ሁሉ የአየር በረራ ጀርባ ሆነው፣ የበረራውን ደህንነት፣ አዋጭነትና ቅልጥፍና የሚቆጣጠሩት #የአየር_ትራፊክ_ተቆጣጣሪዎች ናቸው።
ያለነሱ ከአደጋ ነፃ የሆነ እና የሰመረ የአየር በረራን ማሰብ ከባድ እንደሚሆን ይነገራል።
በዚህም ምክንያት የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ሚናን፣የአቪኤሽን ዘርፍ የልብ ምት ነው እንዲባል ያደርገዋል።

በሌላ በኩል ስራው ባለው ውጥረትና ጭንቀት ምክንያት በዓለም ዙሪያ ከባድ ከሆኑ የሙያ አይነቶች አንዱ ያደርገዋል።
ጥቅምት 10 በዓለም አቀፍ ደረጃ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ስራ የሚታሰብበት፣ተገቢው ክብር የሚሰጥበት ዕለት ነው።
የኢትዮጵያ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ማህበርም ቀኑን አስቦት ውሏል።
በዓለም ዙሪያ በዚህ ሙያ ለተሰማሩት ባለሙያዎች የሚሰጠው ክብርና የሚያገኙት ክፍያ ከፍተኛ መሆኑ የተነሳ ሲሆን በኢትዮጵያ ግን ባለሙያዎቹ ለስራቸው የማይመጥን በጣም ዝቅተኛ ደምወዝ ተከፋይ መሆናቸው ተነግሯል።
ለዚህ ሙያ ከአፍሪካም ዝቅተኛውን ክፍያ የምትከፍለው ሀገር ኢትዮጵያ መሆኗም ሲነገር ሰምተናል።
በዚህም ምክንያት ሰራተኛው በየጊዜው ከተቋሙ ስለሚለቅ ብዙ ልምድ የሚጠይቀው የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪነት ሙያ ልምድ ያለውና ለረጅም ጊዜ የሚያገለግል ባለሙያ እንዲያጣ ሆኗል ተብሏል።
እለቱን ምክንያት በማድረግም ከዚህ ጋር የተገናኙ ለዓመታት የሚነሱ ጥያቄዎች መልስ እንዲያገኙ ተጠይቋል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
ቴዎድሮስ ወርቁ












Comments