top of page

ጥቅምት 11፣2017 - በአማራ ክልል በጦርነት ምክንያት የተፈጠረውን የጤና አገልግሎት እና የሰብዓዊ ድጋፎች ችግር ይፈታል የተባለ ሰነድ መዘጋጀቱ ተሰማ

በአማራ ክልል በጦርነት ምክንያት የተፈጠረውን የጤና አገልግሎት እና የሰብዓዊ ድጋፎች ችግር ይፈታል የተባለ ሰነድ መዘጋጀቱ ተሰማ፡፡


በሰነድ ዝግጅቱ ላይ መንግስትን ጨምሮ የአማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች መሳተፋቸው ተሰምቷል።


አሁን ላይ በአማራ ክልል ያለው ግጭት መሰረታዊ የጤና አገልግሎቱን ለማከናውን ትልቅ ችግር ሆኗል ተብሏል፡፡


የአማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ምሁራን ባደረጉት ውይይት ግጭቱ የማህበረሰቡን የጤና አገልግሎት ወደ ውስብስብ ችግር እንዲገባ ምክንያት ሆኗል ብለዋል፡፡


ከዚህ በተጨማሪም ድጋፍ በክልሉ የትኛውም አካባቢዎች እንዳይደርስ አድርጎታል ሲሉ ለሸገር ኤፍ ኤም ሬድዮ ነግሯል፡፡


የአማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ይህንን ችግር ይፈታል የተባለ ጥናታዊ ሰነድ ማዘጋጀቱን ሰምተናል፡፡፡


የአማራ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ በላይ በዛብህ ክልሉ በጤናው ዘርፍ ትልቅ ችግር ውስጥ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡


ይህም አለማቀፍ ድጋፍን የሚፈልግ ነው ሲሉ አክለዋል።


ባለፉት 5 ዓመታት የአማራ ክልል በሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ በሆነ ችግር ውስጥ መሆኑን ሰሞኑን በተካሄደው የአማራ ክልል የዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ላይ ተነስቷል፡፡


በተዘጋጀው ጥናት ላይ የዓለም የጤና ድርጅት (WHO) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የሲቪክ ማህበራት እንዲሁም የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት በጋራ የተሳተፉበት ነው ተብሏል።


ማርታ በቀለ





Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page