top of page

ጥቅምት 11፣2017 - መብታቸው እንዲጠበቅላቸው በሚከራከሩ መምህራን ላይ እንግልት እና ማዋከብ ይደርስባቸዋል ሲል የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ተናገረ

  • sheger1021fm
  • Oct 21, 2024
  • 1 min read

መብታቸው እንዲጠበቅላቸው በሚከራከሩ መምህራን ላይ እንግልት እና ማዋከብ ይደርስባቸዋል ሲል የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ተናገረ፡፡


ይህ የተነገረው ማህበሩ 37ኛ መደበኛ የምክር ቤት ስብሰባውን በአዳማ ከተማ ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡


በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የሚያስተምሩ #መምህራን እየገጠሟቸው ያሉ ችግሮች በስብሰባው ላይ እንደተነሱ ተነግሯል፡፡

ያለው ከፍተኛ የኑሮ ውድነት መምህራንን እየተፈታተነ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡

ረጅም ጊዜ አገልግሎት ላላቸው መምህራን የደረጃ እድገት የመስጠት ችግር አለ ተብሏል፡፡


በአንዳንድ ክልሎች የመምህራን #ደመወዝ በጊዜ እንደማይከፈል ተነግሯል፡፡


በተጨማሪም መምህራን ደመወዛቸው እየተቆራረጠ በፐርሰንት እንደሚከፈላቸው እንዲሁም ያለመምህራኑ ዕውቅናና ፈቃድ ከደመወዛቸው ይቆረጥባቸዋል ተብሏል፡፡


ይሄንን የሚቃወሙትን ደግሞ ማዋከብና #ማንገላታት እንደሚደርስባቸው አውቄለሁ ብሏል የመምህራን ማህበሩ በማህበራዊ የትስስር ገጹ ላይ አስፍሯል፡፡


ቀደም ብሎ የተጀመረው የመምህራን የመኖሪያ ቤት እና የመሥሪያ ቦታ በሚፈለገው ፍጥነት እየተከናወነ እንዳልሆነም ጠቅሷል፡፡


በትርፍ ሰዓት ክፍያ ላይ ተደራራቢ ግብር መቆረጡ፣ የመጽሐፍትና ሌሎች ግብአቶች እጥረት መኖሩ፣ በክረምት መምህራን ስልጠና ላይ ያለው ክፍተት፤ በዘርፉ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች መሆናቸውን ከደረሱኝ አስተያየቶች ተረድቻለሁም ብሏል፡፡

댓글


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page