በሎጀስቲክስ ማቀላጠፍ ስራ ለተሰማሩ ኢንቨስተሮች የሚደረገው ድጋፍ በጣም ዝቅተኛ መሆኑን ተነገረ፡፡
የኢትዮጵያ የዕቃ አስተላላፊዎችና የመርከብ ወኪሎች ማህበር ምክትል የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አንተነህ አለሙ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶች የሀገሪቱ የወጪና ገቢ እቃ በሚገባ እንዲንቀሳቀስ እያደረጉ ነው ብለዋል፡፡
ነገር ግን ለዘርፉ መንግስት የሚሰጠው የኢንቨስትመንት ማበረታቻ እጅግ ዝቅተኛ መሆኑን አቶ አንተነህ ተናግረዋል፡፡
በዚህ ወቅት ቀይ ባህር አካባቢ ያለው ውጥረት በስራችን ላይ እንቅፋት እየፈጠረ ቢሆንም አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም ስራዎች እየተሰራ ነው ያሉ ሲሆን፤ ማህበሩ በተለያዩ ጊዜ ለመንግስት ጥናቶችን በግሉ በማድረግ የሚታዩ ችግሮችን እየተናገረ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ለማድረግ እየሞከረ ነው ብለዋል፡፡
በሎጀስቲክስ ማቀላጠፍ ዘርፍ ላይ የተሰማራው ባለሃብት በቁጥር በጣም ዝቅተኛ መሆኑን የሚናገሩት አቶ አንተነህ የሚሰጠው ማበረታቻም ዝቅተኛ ነው ሲሉ ያስረዳሉ፡፡
በዚህ ሰዓት የሎጀስቲክስ ስራውን በሚገባ ለመምራትና ገቢና ወጪ ንግዱን ለማቀላጠፍ እንዲረዳ እንደ ሀገር የተሽከርካሪ ኢንቨስትመንት ያስፈልገናል በማለት አሳስበዋል፡፡
የሎጂስቲክስ ዘርፍ ሰፊ የመሬት አቅርቦትና ማሽነሪ መጠቀም የሚፈልግ ዘርፍ ነው ይህንና ሌሎችም በሎጂስቲክስ ዘርፍ የሚታዩ ክፍተቶች በጋራ ተነጋግሮ መፍታት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ...
በረከት አካሉ
Comments