አምስት ዋና ዋና የመልካም አስተዳደር መርህዎችን መሰረት ተደርጎ በተሰራ ልኬት የማዕድን ሚኒስቴር የመጨረሻውን ደረጃ ያዘ፡፡
ልኬቱን የሰራው የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ነው፡፡
ልኬቱ የተሰራው በኢትዮጵያ ካሉ 22 ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ውስጥ በ15ቱ ነው ተብሏል፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ልኬቱን ለማሰናዳት 10 ወር እንደፈጀበት ሲናገር ሰምተናል፡፡
መለኪያ መስፈርቶቹ 5 ሲሆኑ እነሱም ውጤታማነት፣ ተጠያቂነት፣ ግልፅነት፣ ፍትሃዊነትና የህግ ተገዥነት ናቸው መባሉን ሰምተናል፡፡
በተሻለ የአፈፃፀም ደረጃ በቅደም ተከተል የጤና፣ የገንዘብ፣ የግብርና፣ የትምህርት፣ የኢንዱስትሪ እና የፍትህ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ተቀምጠዋል፡፡
15ቱም መስሪያ ቤቶች የመረጃን ነፃነት ህግን አለመተግበር የታየባቸው ክፍተት ነው ተብሏል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments