የጀርመኗ የመከላከያ ሚኒስትር ክርስቲን ላምበሬችት በገዛ ፈቃዳቸው ስልጣናቸውን መልቀቃቸው ተሰማ፡፡
የመከላከያ ሚኒስትሯ ከ2 ሳምታት በፊት በዘመን መለወጫው ባስተላለፉት መልዕክት ለዩክሬይን በጦር እርዳታነት 5000 የወታደር ቆቦችን እንልካለን ማለታቸው ለትችት ዳርጓቸው መቆየቱን ዘጋርዲያን ፅፏል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የጀርመንን ጦር በማዘመኑ ረገድ ዳተኛ ሆነዋል በሚል እየተነቀፉ እንደሆነ በዘገባው ተጠቅሷል፡፡
ከነዚህ ትችቶች በተጨማሪ በጦር ሄሊኮፕተር ልጃቸውን አንሸርሽረዋል መባላቸውም እያስወረፋቸው ነው፡፡
ጀርመን ለዩክሬይን ዘመን አፈራሽ ታንኮችን እንድትሰጥ ጉትጎታ እንደበዛባት ዘገባው አስታውሷል፡፡
የኔነህ ከበደ
ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Comments