top of page

ጥር 9፣ 2015- የአለም የጤና ድርጅት አገሮች የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ (ማስክ) መጠቀምን ዳግም ስራ ላይ ወደማዋሉ እንዲመለሱ መከረ


የአለም የጤና ድርጅት አገሮች የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ /ማስክ/ መጠቀምን ዳግም ስራ ላይ ወደማዋሉ እንዲመለሱ መከረ፡፡


ድርጅቱ ምክሩን የለገሰው በአሁኑ ወቅት የኮቪድ 19 ወረርሽኝ እያገረሸ በመምጣቱ ምክንያት እንደሆነ ቫንጋድ ፅፏል፡፡


የአለም የጤና ድርጅት በቂ አየር በማይገባባቸው እና ሰዎች በብዛት በሚሰባሰቡባቸው ቦታዎች ማስክ የማድረጉን አስፈላጊነት በምክሩ መጥቀሱ ተሰምቷል፡፡


ወቅታዊ ምክሩን ተግባራዊ ማድረጉ የወረርሽኙን መዛመት ለመገደብ ድርሻው የጎላ እንደሚሆን ድርጅቱ ተማምኖበታል ተብሏል፡፡


በበሽታው መያዛቸው በምርመራ የሚረጋገጥ ግለሰቦች በጤና ተቋማት ወይም በቤታቸው ቢያንስ ለ10 ቀናት ተለይተው መሰንበት እንደሚገባቸውም መክሯል፡፡


የኔነህ ከበደ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

댓글


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page